የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽሐፈ ሲራክ 31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽሐፈ ሲራክ 31

ስለ ሕልም ከን​ቱ​ነት

1 ሰነፍ ሰው ግን ሐሰ​ትን በከ​ንቱ ተስፋ ያደ​ር​ጋ​ታል፤ ሕል​ምም ሰነፍ ሰውን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ዋል።

2 ሕል​ምን የሚ​ያ​ምን ሰው ጥላን እን​ደ​ሚ​ጨ​ብጥ፤ ነፋ​ስ​ንም እን​ደ​ሚ​ከ​ተል ነው።

3 ሕልም ከዚህ ወደ​ዚህ ይሄ​ዳል፤ በየ​ም​ሳ​ሌ​ውም የእ​የ​ራ​ሱን ያሳ​ያል።

4 ከር​ኩስ ምን ንጹሕ ይወ​ጣል? ከሐ​ሰ​ትስ እው​ነት ከየት ይገ​ኛል?

5 ሕልም፥ ጥን​ቆ​ላና ሟርት ሁሉም ከንቱ ናቸው፤ ልብ​ንም ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ እንደ ምጥም ያጎ​ብ​ጣሉ።

6 ይቅር ይል ዘንድ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ላከ ከአ​ል​ሆነ፥ በል​ብህ አታ​ኑ​ረው።

7 ሕልም ብዙ ሰዎ​ችን አስ​ት​ዋ​ቸ​ዋ​ልና፤ እር​ሱ​ንም ተስፋ እያ​ደ​ረጉ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና።

8 ያለ ሐሰ​ትስ ከታየ በእ​ው​ነት ይደ​ር​ሳል፤ የእ​ው​ነት ቃልም የተ​ረዳ ይሆ​ናል።

9 የተ​ማረ ሰው ብዙ ምክ​ርን ያው​ቃል፤ ብዙ መከ​ራን የተ​ቀ​በለ ሰውም ጥበ​ብን ያስ​ተ​ም​ራል።

10 ያል​ተ​ነካ ሰው ግን የሚ​ያ​ው​ቀው ነገር የለም።

11 ብዙ መከራ የተ​ቀ​በለ ሰው ብዙ ትም​ህ​ርት ይማ​ራል።

12 መከ​ራን በተ​ቀ​በ​ልሁ ጊዜ ብዙ አየሁ፤ ከአ​ሳ​ቤም ቃሌ በዛ።

13 ለሞት እስ​ክ​ደ​ርስ ድረስ ሁል​ጊዜ መከ​ራን ተቀ​ብ​ያ​ለ​ሁና፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነ​ኛል።

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ ነፍስ ትድ​ና​ለች።

15 እር​ሱን ተስፋ ያደ​ረጉ ሁሉ ይድ​ናሉ።

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰውን የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራው የለም፤ እርሱ አለ​ኝ​ታው ነውና አይ​ደ​ነ​ግ​ጥም።

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ነፍስ ብፅ​ዕት ናት።

18 እርሱ ያድ​ር​በ​ታ​ልና፥ የታ​መነ ወዳ​ጁም ነውና።

19 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖቹ ወደ ወዳ​ጆቹ ናቸው፤ ኀይሉ የታ​መነ ነው፤ ጥግ​ነ​ቱም ጽኑ ነው፤ ቃጠ​ሎ​ውን ያቀ​ዘ​ቅ​ዝ​ል​ሃል፤ ከቀ​ትር ፀሐ​ይም ይጋ​ር​ድ​ሃል፤ ከዕ​ን​ቅ​ፋት ይጠ​ብ​ቅ​ሃል፤ ከመ​ው​ደ​ቅም ይረ​ዳ​ሃል።

20 ሰው​ነ​ት​ህን ያገ​ና​ታል፤ ዓይ​ኖ​ች​ህ​ንም ያበ​ራ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ው​ሳል፤ ደኅ​ን​ነ​ት​ንም ይሰ​ጣል፤ በረ​ከ​ት​ንም ያጠ​ግ​ባል።

21 የበ​ደል መባእ መሥ​ዋ​ዕት ርኩስ ነው፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም ቍር​ባ​ና​ቸው የረ​ከሰ ነው።

22 የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም መባእ ተቀ​ባ​ይ​ነት የለ​ውም።

23 በመ​ባህ ብዛት ኀጢ​አ​ትህ የሚ​ሰ​ረ​ይ​ልህ አይ​ደ​ለም።

24 በዐ​መፃ ገን​ዘብ መባ​እን የሚ​ያ​ገባ ሰው፤ ሕፃ​ንን በአ​ባቱ ፊት እን​ደ​ሚ​ገ​ድል ሰው ነው።

25 የድሃ ሕይ​ወቱ ምጽ​ዋት መለ​መን ነው፤ እምቢ ያለው ሰው ግን ነፍሰ ገዳይ ነው።

26 ባልን ከሚ​ስቱ የሚ​ያ​ፋታ ሰው፥ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን እን​ደ​ሚ​ገ​ድል ሰው ነው።

27 የም​ን​ደ​ኛ​ውን ደመ​ወዝ የቀማ ሰው፥ ደሙን ማፍ​ሰሱ ነው።

28 አንዱ ሲሠራ አንዱ ቢያ​ፈ​ርስ፥ የሁ​ለ​ቱስ ድካ​ማ​ቸው ምን ይጠ​ቅ​ማል?

29 አንዱ ሲመ​ርቅ ሌላው ቢረ​ግም፥ ከሁ​ለቱ የማ​ና​ቸ​ውን ቃል ይሰ​ማል?

30 ሬሳ ከዳ​ሰሰ በኋላ እጁን ቢታ​ጠብ፥ ዳግ​መኛ ሬሳ​ውን ከዳ​ሰሰ መታ​ጠቡ ምን ይጠ​ቅ​መ​ዋል?

31 እን​ዲሁ ስለ ኀጢ​አቱ የሚ​ጾም ሰው ዳግ​መኛ ይበ​ድል ዘንድ ከሄደ፥ ከዚህ በኋላ ጸሎ​ቱን ማን ይሰ​ማ​ዋል? ሰው​ነ​ቱ​ንስ ማሳ​ዘኑ ምን ይጠ​ቅ​መ​ዋል?