የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽ​ሐፈ ዕዝራ ሱቱ​ኤል 9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽ​ሐፈ ዕዝራ ሱቱ​ኤል 9

1 “ከዚህ በኋላ ወደ ጫጕ​ላው በገባ ጊዜ ወድቆ ሞተ።

2 ከዚህ በኋ​ላም ፋና​ች​ን​ንና መብ​ራ​ታ​ች​ንን አጠ​ፋን፤ እና​ለ​ቅስ ዘን​ድም ተቀ​መ​ጥን፤ ያገሬ ሰዎ​ችም ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ይመ​ክ​ሩ​ኝና ያረ​ጋ​ጉኝ ጀመሩ፤ ከዚ​ህም በኋላ እስከ ማግ​ሥ​ትዋ ቀን ሌሊት ድረስ ዝም አልሁ።

3 ከዚህ በኋላ ሁሉም ዝም ባሉ ጊዜ፥ እኔ​ንም መም​ከር በተዉ ጊዜ እኔ ሌሊት ተነ​ሥቼ ሸሸሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ምድረ በዳ መጣሁ።

4 ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ በዚሁ እኖ​ራ​ለሁ እንጂ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ ሀገሬ እን​ዳ​ል​መ​ለስ ቈረ​ጥሁ፤ ሁል​ጊዜ እጾ​ማ​ለሁ፤ እስ​ክ​ሞ​ትም ድረስ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ እንጂ እህል አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም።”

5 ያ የማ​ስ​በው አሳ​ቤም ተወኝ፤ እኔም መለ​ስ​ሁ​ላት፤ እን​ዲ​ህም አል​ኋት፦

6 “ከሴ​ቶች ሁሉ አንቺ አላ​ዋቂ ነሽ፤ ያገ​ኘ​ች​ንን የእ​ኛን ልቅሶ አታ​ዪ​ምን?

7 ስለ ሁላ​ችን እናት ስለ ጽዮን ሁላ​ችን በኀ​ዘን አለን፤ መከ​ራ​ንም ፈጽ​መን ተቀ​በ​ልን።

8 አሁ​ንም በእ​ው​ነት ታዝ​ኚና ታለ​ቅሺ ዘንድ ይገ​ባ​ሻል፤ እኛ ሁላ​ች​ንም ያዘ​ንን ነንና፤ እኛም ስለ ብዙ​ዎች እና​ዝ​ና​ለን፤ አንቺ ግን ስለ አንዱ ልጅሽ ታዝ​ኛ​ለሽ።

9 ምድ​ርን ጠይ​ቂ​አት፤ ትነ​ግ​ር​ሻ​ለ​ችም፤ በእ​ር​ስዋ ላይ ይህን ያህል ስለ ተወ​ለ​ዱት ታለ​ቅስ ዘንድ አግ​ባብ ለእ​ር​ስዋ ነው።

10 ሁሉም ከጥ​ንት ጀምሮ በእ​ር​ስዋ ላይ ተፈ​ጠሩ። እነ​ሆም ሌሎች መጥ​ተው ሁሉ​ንም በሙሉ ፈጽሞ ለማ​ጥ​ፋት ወሰ​ዷ​ቸው።

11 እን​ግ​ዲህ ወዲህ ፈጽሞ ያለ​ቅስ ዘንድ የሚ​ገ​ባው ማን ነው? ይህን ያህል ብዙ የጠ​ፋ​በት ነውን? ወይስ አንቺ ስለ አንድ ልጅሽ ታዝ​ኛ​ለ​ሽን?

12 ወይስ በጻ​ዕ​ርና በገ​ዓር የወ​ለ​ድ​ሁ​ትን ልጄን አጥ​ቻ​ለ​ሁና፤ የእኔ ልቅሶ እንደ ምድር ልቅሶ አይ​ደ​ለም ትያ​ለ​ሽን?

13 ምድር ግን ብዙ አሕ​ዛብ ወደ እርሷ እንደ መጡ እን​ደ​ዚሁ ሄዱ።

14 ነገር ግን እኔ እን​ዲሁ እል​ሻ​ለሁ፤ አንቺ አም​ጠሽ እንደ ወለ​ድሽ እን​ዲ​ሁም ምድር ከጥ​ንት ጀምሮ በእ​ርሷ ለተ​ፈ​ጠሩ ሰዎች ፈጣ​ሪዋ የሰ​ጣ​ትን ፍሬ​ዋን ሰጠ​ቻ​ቸው።

15 አሁ​ንም ይህን ኀዘ​ን​ሽን ካንቺ አርቂ፤ ስለ አገ​ኘ​ችሽ ቅጣ​ትና መከ​ራም ትዕ​ግ​ሥ​ተኛ ሁኚ።

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብታ​መ​ሰ​ግ​ኚው ይረ​ዳ​ሻ​ልና፥ ልጅ​ሽ​ንም በጊ​ዜው ታገ​ኚ​ዋ​ለ​ሽና፥ በሴ​ቶ​ችም ዘንድ መከ​ራን የታ​ገ​ሠች ትባ​ያ​ለ​ሽና፥

17 አሁ​ንም ወደ ሀገ​ርሽ ግቢ፤ ወደ ባል​ሽም ሂጂ።”

18 እር​ስ​ዋም አለ​ችኝ፥ “እን​ዲ​ህስ አላ​ደ​ር​ግም፤ በዚህ እሞ​ታ​ለሁ እንጂ ወደ ሀገሬ አል​ገ​ባም።”

19 ዳግ​መ​ኛም ተና​ገ​ር​ኋት፤ እን​ዲ​ህም አል​ኋት፦

20 “ይህን ነገር አታ​ድ​ርጊ፤ እሺ በዪኝ፤ ራስ​ሽ​ንም እንደ ጽዮን መከራ አድ​ርጊ፤ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ከተማ ተረ​ጋጊ።

21 ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ችን እንደ ፈረሰ፥ መሠ​ዊ​ያ​ችን እንደ ተሰ​ባ​በረ አታ​ዪ​ምን?

22 ግና​ያቱ እንደ ጠፋ፥ ምስ​ጋ​ና​ችን እንደ ቀረ፥ ዘመራ ዘው​ዳ​ችን እንደ ወደቀ፥ የመ​ቅ​ረ​ዛ​ችን መብ​ራት እንደ ጠፋ፥ የቃል ኪዳ​ና​ችን ታቦት እንደ ተማ​ረ​ከች፥ ንዋየ ቅድ​ሳ​ታ​ችን እን​ዳ​ደፈ፥ ስማ​ችን እንደ ረከሰ፥ ጌቶ​ቻ​ችን እንደ ተዋ​ረዱ፥ ካህ​ኖ​ቻ​ችን እንደ ተቃ​ጠሉ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኖ​ቻ​ችን እንደ ተማ​ረኩ፥ ደና​ግ​ሎ​ቻ​ችን እንደ ተገ​ደሉ፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ንን እንደ ቀሙን፥ ጻድ​ቃ​ኖ​ቻ​ችን እንደ ተጐ​ተቱ፥ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ችን እንደ ተገዙ፥ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ችን እንደ ተቀሙ፥ አር​በ​ኞ​ቻ​ችን እንደ ደከሙ አታ​ዪ​ምን?

23 ከዚህ ሁሉ የሚ​በ​ልጥ ጽዮን ጠፋች፤ ክብ​ር​ዋም ከእ​ር​ስዋ ወጣ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እጅ ወደ​ቅን።

24 አን​ቺም ተዪ፥ ልዑ​ልና ኀያል ይቅር ይልሽ ዘንድ፥ ከድ​ካ​ም​ሽም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ ያሳ​ር​ፍሽ ዘንድ ይህን ብዙ ኀዘ​ን​ሽን አርቂ።”

25 ከዚህ በኋላ ይኽን ስና​ገ​ራት ድን​ገት ፊትዋ ከፀ​ሐይ ይልቅ በራ፤ መል​ኳም እንደ መብ​ረቅ አን​ጸ​ባ​ረቀ፤ ወደ እርሷ መቅ​ረ​ብ​ንም ፈራሁ፤ ልቡ​ና​ዬም ደነ​ገ​ጠ​ብኝ፤ ከዚ​ህም በኋላ ይህ ምን እንደ ሆነ ሳስብ አስ​ደ​ነ​ገ​ጠ​ችኝ።

26 በታ​ላቅ ድም​ፅም ጮኸች፤ ከድ​ም​ፅ​ዋም የተ​ነሣ ምድር እስ​ክ​ት​ነ​ዋ​ወጥ ድረስ ድም​ፅዋ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ሆነ።

27 ባየ​ኋ​ትም ጊዜ እነሆ የከ​በ​ረ​ችና የታ​ነ​ጸች ከተማ ነበ​ረች እንጂ ሴት አል​ነ​በ​ረ​ችም፤ ታላቅ የሆነ የመ​ሠ​ረ​ቶ​ች​ዋ​ንም ቦታ አየሁ፤ ፈር​ቼም በታ​ላቅ ድምፅ ጮህኹ። እን​ዲ​ህም አልሁ፦

28 “አስ​ቀ​ድሞ ወደ እኔ የመ​ጣህ መል​አኩ ዑር​ኤል፥ አንተ ወዴት ነህ? ወደ ብዙ ምር​ምር እገባ ዘንድ፥ ፍጻ​ሜ​ዬም ለጕ​ስ​ቍ​ል​ናዬ ትሆን ዘንድ፥ ጸሎ​ቴም ለተ​ግ​ዳ​ሮት ይሆን ዘንድ እን​ዲህ ለምን አደ​ረ​ግ​ኸኝ?”

የራ​እዩ ትር​ጓሜ

29 እኔ እን​ደ​ዚህ ስና​ገር እነሆ፥ ቀድሞ ወድ እኔ የመ​ጣው ያ መል​አክ ወደ እኔ መጣ።

30 እንደ ሬሳ ተኝቼ አገ​ኘኝ፤ አእ​ም​ሮ​ዬም ከእኔ ጋር አል​ነ​በ​ረም፤ ቀኝ እጄ​ንም ይዞ አጸ​ናኝ፤ በእ​ግ​ሮ​ችም አቅ​ንቶ አቆ​መኝ።

31 መለ​ሰ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ምን ሆንህ? ምንስ ያስ​ደ​ነ​ግ​ጥ​ሃል? ልብ​ህስ ካንተ ጋር ስለ​ምን የለም?”

32 እኔም አል​ሁት፥ “አንተ ጥለ​ኸ​ኛ​ልና፥ ተለ​ይ​ተ​ኸ​ኛ​ል​ምና፥ እኔ እንደ ነገ​ር​ኸኝ ወደ​ዚህ ምድረ በዳ መጣሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ምድረ በዳ በመ​ጣሁ ጊዜ እነሆ፥ ማወቅ የማ​ይ​ቻ​ለ​ኝን አየሁ።”

33 እር​ሱም አለኝ፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ እነ​ግ​ርህ ዘንድ እንደ ሰው ቁም።”

34 እኔም አቤቱ ተና​ገር አል​ሁት፥ “ድን​ገት እን​ዳ​ል​ሞት እን​ግ​ዲህ አት​ለ​የኝ እንጂ።

35 ያላ​የ​ሁ​ትን አይ​ቻ​ለ​ሁና፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ሰም​ቻ​ለ​ሁና።

36 ነገር ግን ምና​ል​ባት ልቡ​ናዬ ይዘ​ነጋ ይሆ​ንን? ሰው​ነ​ቴስ ትጨ​ነቅ ይሆ​ንን?

37 አሁ​ንም አቤቱ በጅ በለኝ፤ የዚ​ህ​ንም ራእይ ትር​ጓሜ ለባ​ሪ​ያህ ንገ​ረው።”

38 እር​ሱም መለ​ሰ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ስለ​ም​ት​ፈ​ራው ነገር አስ​ተ​ም​ርህ ዘንድ ስማኝ። ይህ የተ​ሰ​ወረ ምሥ​ጢር ስለ​ሆነ፦ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገል​ጦ​ል​ሃ​ልና።

39 ጽድ​ቅ​ህ​ንም አየ፤ ስለ ወገ​ኖ​ችህ ብዙ ታዝ​ና​ለ​ህና፤ ስለ ጽዮ​ንም እጅግ ትቈ​ረ​ቈ​ራ​ለ​ህና።

40 ነገሩ ይህ ነው፦

41 ቀድሞ እንደ አል​ቃሽ ሆና ያየ​ሃት፥ ታረ​ጋ​ጋ​ትም ዘንድ የጀ​መ​ርህ ይች ሴት፥

42 አሁን አንተ እን​ዳ​የ​ሃት ሴት አይ​ደ​ለ​ችም። የታ​ነ​ጸች ከተማ እንጂ።

43 ስለ ልጅዋ መከራ ነግ​ራ​ሃ​ለ​ችና።

44 ያች ያየ​ሃት ሴት ዛሬ እንደ ታነ​ጸች ከተማ ሀገር ሁና የም​ታ​ያት ጽዮን ናት።

45 ሠላሳ ዘመን መካን ሆንኹ ያለ​ች​ህም ይህ ነው፤ የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት መሥ​ዋ​ዕት ሳይ​ኖር ዓለም ሦስት ሺህ ዘመን ኖሯ​ልና።

46 ከሦ​ስት ሺህ ዓመት በኋ​ላም ሰሎ​ሞን ከተ​ማን ሠራ፤ ያን​ጊ​ዜም ቍር​ባ​ንን አቀ​ረበ። ያችም መካን ሴት የወ​ለ​ደ​ችው ልጅ፥

47 ይህም በብዙ ድካም አሳ​ደ​ግ​ሁት ያለ​ችህ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የኖ​ረ​ችው ዘመን ነው።

48 ይህም ልጅዋ ወደ ጫጕ​ላው በገባ ጊዜ ወድቆ ሞተ፤ ይህም መከራ አገ​ኘን ያለ​ችህ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጥፋ​ትዋ ነው።

49 እነሆ ለል​ጆ​ችዋ እን​ዴት እን​ደ​ም​ታ​ለ​ቅ​ስ​ላ​ቸው ያየ​ሃት፥ አን​ተም ከመ​ከ​ራዋ ታረ​ጋ​ጋት ዘንድ የጀ​መ​ርህ ያች ሴት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ናት።

50 አሁ​ንም ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እር​ስዋ በፍ​ጹም ሰው​ነ​ትህ እን​ድ​ታ​ዝን፥ በፍ​ጹም ልቡ​ና​ህም እን​ድ​ት​ቈ​ረ​ቈር ባየ ጊዜ የደ​ስ​ታ​ዋን ጌጥና የክ​ብ​ሩ​ዋን መገ​ለጥ አሳ​የህ። የተ​ሰ​ወረ ምሥ​ጢር ነውና።

51 ስለ​ዚህ ነገር ቤት ባል​ተ​ሠ​ራ​በት በዚህ በም​ድረ በዳ ትኖር ዘንድ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።

52 ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ይህ ዘንድ ያለ​ውን ሁሉ አው​ቄ​አ​ለ​ሁና።

53 ስለ​ዚ​ህም የግ​ንብ መሠ​ረት ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ​ዚህ ትመጣ ዘንድ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።

54 ልዑል ይገ​ለ​ጥ​በት ዘንድ ባለው ቦታ የሰው ሥራ ግንብ ሊኖር አይ​ቻ​ል​ምና።

55 “አን​ተስ እን​ግ​ዲህ አት​ፍራ፤ ልብ​ህም አይ​ደ​ን​ግጥ፤ ገብ​ተህ ብር​ሃ​ን​ዋ​ንና የግ​ን​ብ​ዋን ጽናት እይ እንጂ።

56 መስ​ማት የም​ት​ች​ለ​ውን ያህል በጆ​ሮህ ስማ።

57 አንተ ከብ​ዙ​ዎች ይልቅ ራስ​ህን ብፁዕ አሰ​ኝ​ተ​ሃ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ዘንድ እንደ ጥቂ​ቶች ተጠ​ር​ተ​ሃ​ልና።

58 ዛሬም በዚህ እደር።

59 ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ለም በሚ​ኖሩ ሰዎች ላይ በጊ​ዜው የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ራእይ ነገ በሕ​ልም ያሳ​ይ​ሃል።”

60 በዚ​ያ​ችም ሌሊት፥ በማ​ግ​ሥ​ቱም እን​ዳ​ዘ​ዘኝ አደ​ርሁ።