የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሶፎንያስ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጋዛ ትበረበራለች፥ አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች፣ አዛጦንንም በቀትር ወደ ውጭ ያሳድዱአታል፥ አቃሮንም ትነቀላለች።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤ አስቀሎናም ፈራርሳ ትቀራለች፤ አዛጦን በቀትር ባዶ ትሆናለች፤ አቃሮንም ትነቀላለች።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጋዛ ሰው የማይኖርባት ትሆናለች፥ አስቀሎናም ትፈራርሳለች፤ አሽዶድ በቀትር ወደ ውጭ ያሳድዷታል፥ ዔቅሮንም ትነቀላለች።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጋዛ ተለቃ ሰው የማይኖርባት ትሆናለች፤ አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች፤ የአሽዶድ ነዋሪዎች በቀትር ከመኖሪያቸው ይባረራሉ፤ የዓቃሮንም ሰዎች ከከተማይቱ ተፈናቅለው ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጋዛ ትበረበራለች፥ አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች፥ አዛጦንንም በቀትር ወደ ውጭ ያሳድዱአታል፥ አቃሮንም ትነቀላለች።

ምዕራፉን ተመልከት



ሶፎንያስ 2:4
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰነፍ ሰው አያ​ው​ቅም፥ ልብ የሌ​ለ​ውም ይህን አያ​ስ​ተ​ው​ለ​ውም።


ፍል​ስ​ጥ​ኤም ሆይ፥ ከእ​ባቡ ዘር እፉ​ኝት ይወ​ጣ​ልና፥ ፍሬ​ውም የሚ​በ​ር​ርና እሳት የሚ​መ​ስል እባብ ይሆ​ና​ልና፥ የኀ​ይ​ላ​ችሁ ቀን​በር ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ሁላ​ች​ሁም ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ።


መበ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከባ​ሕር አሸዋ ይልቅ በዝ​ተ​ዋል፤ በብ​ላ​ቴ​ኖች እናት ላይ በቀ​ትር ጊዜ አጥ​ፊ​ውን አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ ጭን​ቀ​ት​ንና ድን​ጋ​ጤን በድ​ን​ገት አም​ጥ​ቼ​ባ​ታ​ለሁ።


የተ​ደ​ባ​ለ​ቀ​ው​ንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ምድር ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፤ አስ​ቀ​ሎ​ና​ንም፥ ጋዛ​ንም፥ አቃ​ሮ​ን​ንም፥ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንም ቅሬታ፤


በእ​ር​ስዋ ላይ ሰልፍ አዘ​ጋጁ፤ ተነሡ፥ በቀ​ት​ርም እን​ውጣ። ቀኑ መሽ​ቶ​አ​ልና፥ የቀ​ኑም ጥላ አል​ፎ​አ​ልና ወዮ​ልን።