ከቍጡ ሰው ጋር አትከራከር፤ በእርሱ ዘንድ ደም ማፍሰስ እንደ ኢምንት ነውና፥ ረዳት ወደሌለበት ቦታም ይወስድሃልና ከእርሱ ጋር ወደ ምድረ በዳ አትውጣ።
ከቁጡ ሰው ጋር አትከራከር፤ ሰዎች በሌሉበት ከሱ ጋር አትሂድ፥ ደም መፍሰስ ለእርሱ ምኑም አይደለምና፤ ሰው በሌለበት ሊጎዳህ ይችላል።