የዘለዓለም ሕግንም አጸናለት፤ በሕዝቡም መካከል ክህነትን ሰጠው፤ በአማረ ጌጥም አስደነቀው፤ የክብር ልብስንም አለበሰው።
ከሌዌ ነገድ የሆነ ወንድሙን፥ እንደ እርሱ የተቀደሰውን አሮንን አስነሣ። ከእርሱም ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አደረገ፥ ሕዝቡን እንዲያገለግልም ክህነትን ሰጠው። በልብሰ ተክህኖ አንቆጠቆጠው፤ የክብርም ካባ አጐናጸፈው።