ሌሊቱ ቀን የሚሆንባቸው ጠራቢና የጠራቢዎች አለቃ፥ የማኅተም ቅርጽ የሚቀርጹና የሚያለዝቡ ሰዎች እንደ እርሱ ናቸው፤ እነዚህም አሳባቸው ሁሉ በየመልኩ መስለው ይሠሩ ዘንድ ነው፤ ምክራቸውም ሁሉ ማኅተሙን ማለዘብን ይጠነቀቁ ዘንድ ነው፤ ትጋታቸውም ሥራቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ነው።
ሠራተኞችና የእጅ ባለሙያዎችም፥ ቀን ከሌት ይደክማሉና እንዲሁ ናቸው። ማኀተሞች የሚቀርጹ፥ አዳዲስ ንድፋቸውንም መልሰው የሚቀርጹ፥ ሥራቸውንም ለማጠናቀቅ ሌትም የሚሠሩ፤ ባተሌዎች በመሆናቸው ጥበብን ለመቅሰም ጊዜ አይኖራቸውም።