ከዚህ በኋላ ልቅሶህን ተው። ኀዘንም አይግባህ፤ በኀዘን የሞቱ ብዙዎች ናቸውና፥ የልብ ኀዘንም ኀይልን ይሰብራልና።
መሪር ኀዘን ሞትን ያመጣል፤ ሰቆቃ የበዛበት ልብም ትደክማለችና።