እስኪበደርህ ድረስ ራስህን ይስምሃል፤ ቃሉንም ያለሰልሳል፤ ገንዘብህንም እስኪወስድ ድረስ ያባብልሃል፤ በሚከፍልበት ጊዜ ግን ቀጠሮህን ያረዝምብሃል፤ በገንዘብህም ጠብና ክርክርን ይከፍልሃል፤ ያደክምሃል፤ ቀጠሮህንም ያሳልፋል።
ሰው የሚፈልገውን እስኪያገኝ የባልንጀራውን እጅ ይስማል፤ ስለ አበዳሪውም ሀብት በትሕትና ይናገራል። የመክፈያው ጊዜ ሲደርስ ግን ቀኑን ያስተላልፋል፤ እንዳመጣለት ይናገራል፤ ጊዜውም እንዲራዘምለት ይጠይቃል።