ለድሃ መልካም አድርግ፥ ለክፉ ግን አትስጥ፤ እርሱ እንዳይወስድብህና በገንዘብህ ድል እንዳያደርግህ እንጀራህን ከልክለው፥ በጎ ነገር ስላደረግህለት ፋንታ በእርሱ ዘንድ ክፋትን እጥፍ ሆና ታገኛታለህና።
ለትሑት ሰው ደግ አድርግ፥ ለክፉ ሰው ምንም አትስጥ፤ እንጀራም ከልክለው፥ ምንም አትስጠው፥ ከሰጠኸው ግን በአንተ ላይ ኃይል ያገኛል፤ ባደረግህለት ደግ ሥራ ሁሉ ዕጥፍ ክፋት ያደርግብሃል።