የሰው ዘር የከበረ ዘር ነው፥ የከበረ ዘር ማንነው? እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ዘር አይደለምን?
የትኛው ዘር ነው ክብር የሚገባው? ክብር የሚገባው የሰው ዘር ነው። ክብር የሚገባው የትኛው ዘር ነው? ክብር የሚገባው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነው። መወገዝ የሚገባው የትኛው ዘር ነው? የሰው ዘር ነው። መወገዝ የሚገባው ዘር የትኛው ነው? የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያፈርሰው ነው።