እንዳቷረድ ሰውነትህም እንዳትወድቅ ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ እግዚአብሔርም የሰወርኸውን ይገልጥብሃል። እግዚአብሔርን በመፍራት አልመጣህምና፥ በልብህም ሽንገላ ሞልትዋልና በብዙዎች ሰዎች መካከል ይጥልሃል።
እንዳትወድቅና በራስህ ላይ ውርደትን እንዳታመጣ ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ። ልብህ በተንኮል በመሞላቱና ጌታን ባለመፍራትህ እርሱ ምሥጢርህን ይገልጥብሃል፤ በሕዝቡም መሀል ያዋርድሀል።