ዋርሳዪቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል’ ስትል የአንድ እግሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊቱም እንትፍ ትበልበት።
ሩት 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቅርብ ዘመዱም ቦዔዝን፦ አንተ ግዛው አለው፣ ጫማውንም አወለቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅድሚያ ያለው ቅርብ የሥጋ ዘመድም ቦዔዝን፣ “እንግዲህ አንተው ራስህ ግዛው” ብሎ ጫማውን አወለቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቅርብ ዘመዱም ቦዔዝን፦ “አንተ ግዛው” አለው፤ ጫማውንም አወለቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሰውየው ቦዔዝን “አንተ ልታስቀረው ትችላለህ” ብሎ ጫማውን አውልቆ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቅርብ ዘመዱም ቦዔዝን “አንተ ግዛው” አለው፤ ጫማውንም አወለቀ። |
ዋርሳዪቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል’ ስትል የአንድ እግሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊቱም እንትፍ ትበልበት።
በጥንት ጊዜም፥ ማንም ቢሸጥ ቢለውጥም፥ ነገሩን ለማጽናት ሰው ጫማውን እንዲያወልቅ ለባልንጀራውም እንዲሰጠው በእስራኤል ዘንድ ልማድ ነበረ። ይህም በእስራኤል ምስክር ነበረ።
ቦዔዝም ሽማግሌዎችንና ሕዝቡን ሁሉ፦ ለአቤሜሌክና ለኬሌዎን ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እንደ ገዛሁ እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ።