የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 91:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ፥ በሥ​ራህ ደስ አሰ​ኝ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፤ በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ደስ ይለ​ኛ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ ከክንፎቹም በታች ትጠለላለህ፥ ታማኝነቱ እንደ ጋሻና እንደ ቅጥር ይከብብሃል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በጥበቃው ሥር ያደርግሃል። እርሱ ስለሚንከባከብህ በሰላም ትኖራለህ፤ የእርሱ ታማኝነት እንደ ጋሻ ወይም እንደ ከተማ ቅጽር ይሆንልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 91:4
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚ​ህም ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በራ​እይ ወደ አብ​ራም መጣ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አብ​ራም ሆይ፥ አት​ፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዋጋ​ህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”


አንተ መቀ​መ​ጤ​ንና መነ​ሣ​ቴን ታው​ቃ​ለህ። የል​ቤን ዐሳብ ሁሉ ከሩቁ ታስ​ተ​ው​ላ​ለህ።


ከቍ​ጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊ​ቱም እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእ​ርሱ በራ።


በአ​ን​ደ​በቱ ሸን​ግ​ሎ​አ​ልና፤ ኀጢ​አቱ ባገ​ኘ​ችው ጊዜ ይጠ​ላ​ታል።


በእ​ው​ነት ጽድ​ቅን ብት​ና​ገ​ሩስ፥ የሰው ልጆች ሆይ፥ በቅን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤


ነገር ግን ክብ​ሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፥ በጥ​ሜም ሮጥሁ፤ በአ​ፋ​ቸው ይባ​ር​ካሉ፥ በል​ባ​ቸ​ውም ይረ​ግ​ማሉ።


“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ንስር ጫጩ​ቶ​ቹን በክ​ን​ፎቹ በታች እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስብ፥ በጎ​ኑም እን​ደ​ሚ​ያ​ቅፍ፥ በክ​ን​ፎቹ አዘ​ላ​ቸው፤ በደ​ረ​ቱም ተሸ​ከ​ማ​ቸው።


እግዚአብሔር እንደ ሥራሽ ይስጥሽ፣ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት።