የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 88:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እው​ነ​ትም ይከ​ብ​ብ​ሃል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሚቀርቡኝ ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅህ፤ እንዲጸየፉኝም አደረግህ፤ ተከብቤአለሁ፤ ማምለጥም አልችልም፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእኔ ላይ ቁጣህ ጸና፥ ማዕበልህንም ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወዳጆቼ ሁሉ ከእኔ እንዲርቁ አደረግህ፤ በፊታቸውም አጸያፊ አደረግኸኝ፤ ዙሪያዬ ታጥሮአል፤ ማምለጫም የለኝም።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 88:8
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ እርሱ ቢያ​ፈ​ርስ፥ ማን ይሠ​ራል? በሰ​ውም ላይ ቢዘ​ጋ​በት ማን ይከ​ፍ​ታል?


ዙሪ​ያዬ ታጥ​ሯል፤ መተ​ላ​ለ​ፊ​ያም የለ​ኝም፤ በፊ​ቴም ጨለ​ማን ጋር​ዶ​በ​ታል።


ተጸ​የ​ፉኝ፥ ከእ​ኔም ራቁ፤ ምራ​ቃ​ቸ​ው​ንም በፊቴ መት​ፋ​ትን አል​ታ​ከ​ቱም።


ሰው​ነቴ በላዬ አለ​ቀ​ች​ብኝ፥ ልቤም በው​ስጤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።


ሰው ከንቱ ነገ​ርን ይመ​ስ​ላል፤ ዘመ​ኑም እንደ ጥላ ያል​ፋል።


ጻድ​ቃን ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጉ፤ ልባ​ች​ሁም የቀና ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ተመኩ።


ረድ​ኤ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። ንጉ​ሣ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነውና።


ታዳ​ጊህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕይ​ወ​ቱን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ትን፥ በአ​ሕ​ዛብ የተ​ጠ​ላ​ውን የአ​ለ​ቆ​ችን ባርያ ቀድ​ሱት፤ ነገ​ሥ​ታት ያዩ​ታል፤ አለ​ቆ​ችም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብለው ተነ​ሥ​ተው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መር​ጨ​ሃ​ለ​ሁና።”


መጭ​መ​ቂ​ያ​ውን ብቻ​ዬን ረግ​ጫ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አል​ነ​በ​ረም፤ በቍ​ጣ​ዬም ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ በመ​ዓ​ቴም ወደ መሬት ጣል​ጥ​ህ​ዋ​ቸው፤ ደማ​ቸ​ው​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰ​ስሁ፤ ልብ​ሴም ሁሉ በደም ታለለ።


በዚያ ጊዜም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት በነ​በ​ረው በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ታስሮ ነበር።


በአንድ ወርም ሦስቱን እረኞች አጠፋሁ፣ ነፍሴም ተሰቀቀቻቸው፥ ነፍሳቸውም ደግሞ እኔን ጠላች።


የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ያለ​በ​ትን የሚ​ያ​ውቅ ቢኖር ይይ​ዙት ዘንድ እን​ዲ​ያ​መ​ለ​ክ​ታ​ቸው አዘዙ።