የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 88:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ፥ ሰማ​ያት ክብ​ር​ህን ጽድ​ቅ​ህ​ንም ደግሞ በቅ​ዱ​ሳን ማኅ​በር ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሙታን መካከል እንደ ተጣሉ፣ ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደ ተጋደሙ፣ አንተ ከእንግዲህ እንደማታስባቸው፣ ከእጅህም ወጥተው እንደ ተወገዱ ሆንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቈጠርሁ፥ ረዳትም እንደሌለው ሰው ሆንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሙታን መካከል ፈጽሞ እንደ ተተዉ፥ ተገድለው በመቃብር እንደ ተጋደሙ፥ ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውና የአንተ እንክብካቤ ከእነርሱ እንደ ተቋረጠ ሰዎች መስዬአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 88:5
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ዚ​ያን ከተ​ሞ​ችና ሎጥ የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ ባጠፋ ጊዜ አብ​ር​ሃ​ምን ዐሰ​በው፤ ሎጥ​ንም ከጥ​ፋት መካ​ከል አወ​ጣው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ በመ​ር​ከ​ብም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን አራ​ዊ​ቱን ሁሉ፥ እን​ስ​ሳ​ው​ንም ሁሉ፥ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ፥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ ነፋ​ስን አመጣ፤ ውኃ​ውም ጐደለ፤


እርሱ ሁሉን ቢገ​ለ​ብጥ፥ ምን አደ​ረ​ግህ? የሚ​ለው ማን ነው?


ነፍ​ሴን የሚ​ያ​ወ​ጣት ያስ​ጨ​ን​ቀ​ኛል መቃ​ብ​ር​ንም እመ​ኘ​ዋ​ለሁ፤ ግን አላ​ገ​ኘ​ውም፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያቈ​ስ​ለኝ ዘንድ ጀመረ፥ ነገር ግን እስከ መጨ​ረ​ሻው አላ​ጠ​ፋ​ኝም።


የአ​ማ​ል​ክት ልጆች ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥ የጊ​ደ​ሮ​ችን ጥጃ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ። ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥


በስ​ምህ ቀኑን ሁሉ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም ከፍ ከፍ ይላሉ፤


በው​ር​ደቱ ፍርዱ ተወ​ገደ፤ ሕይ​ወቱ ከም​ድር ተወ​ግ​ዷ​ልና ልደ​ቱን ማን ይና​ገ​ራል? ስለ ሕዝቤ ኀጢ​አት ለሞት ደረሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥ​ን​ቶ​ቻ​ችን ደር​ቀ​ዋል፤ ተስ​ፋ​ች​ንም ጠፍ​ቶ​አል፤ ፈጽ​መ​ንም ተቈ​ር​ጠ​ናል ብለ​ዋል።