መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥ የቍጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው።
አምላክ ሆይ፤ የክብር አካሄድህ ታየ፤ ይህም አምላኬና ንጉሤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያደርገው የክብር አካሄድ ነው።
እግሮችህ በደም ይረገጡ ዘንድ፥ የውሾችህ ምላስ በጠላቶች ላይ ይሆን ዘንድ።
አምላክ ሆይ! የድል አድራጊነትህ ሰልፍ በሁሉም ይታያል፤ የእኔ ንጉሥና አምላክ በክብር አጀብ ወደ መቅደሱ ሲገባ ይታያል።
ዳዊትና እስራኤል ሁሉ ከመዘምራን ጋር በበገና፥ በመሰንቆና በከበሮ፥ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይዘምሩ ነበር።
ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፤ አቤቱ፥ አምላኬና ረዳቴ፥ በኀይልህ በትናቸው፥ አዋርዳቸውም።
ከክፉዎች ሴራ ከብዙዎች ዐመፅ አድራጊዎች ሰውረኝ።