መዝሙር 68:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመብሌ ውስጥ ሐሞትን ጨመሩ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤን አጠጡኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ፣ በኀጢአታቸውም የሚጸኑትን ሰዎች ጠጕራም ዐናት ይፈነካክታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላካችንስ የሚያድን አምላክ ነው፥ ከሞት ማምለጫውም ከጌታ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርግጥ እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ ይቀጠቅጣል፤ በጠጒር የተሸፈነ አናታቸውን ይሰባብራል።” |
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”
ለሚናገረው እንቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነርሱ በደብረ ሲና የተገለጠላቸውን እንቢ ስለ አሉት ካልዳኑ፥ ከሰማይ ከመጣው ፊታችንን ብንመልስ እኛማ እንዴታ?