የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 65:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሕ​ዛብ ሆይ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንን አመ​ስ​ግኑ፥ የም​ስ​ጋ​ና​ው​ንም ቃል አድ​ምጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ርቀው በምድር ዳርቻ ያሉት ከድንቅ ሥራህ የተነሣ ይደነግጣሉ፤ የንጋትንና የምሽትን መምጫዎች፣ በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋቸዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የባሕሩን ማጓራት፥ የሞገድንም ጩኸት፥ የአሕዛብንም ማጉረምረም ዝም ታሰኛለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስላደረግሃቸው ተአምራት ዓለም በሙሉ በፍርሃት ይዋጣል፤ በአንተ ድንቅ ሥራ ምክንያት ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ የእልልታ ድምፅ ይሰማል።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 65:8
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በም​ድር ዘመን ሁሉ መዝ​ራ​ትና ማጨድ፥ ብር​ድና ሙቀት፥ በጋና ክረ​ምት፥ ቀንና ሌሊት አያ​ቋ​ር​ጡም።”


“የን​ጋት ወገ​ግታ በአ​ንተ ተፈ​ጥ​ሮ​አ​ልን? የአ​ጥ​ቢያ ኮከ​ብስ ትእ​ዛ​ዙን በአ​ንተ ዐው​ቋ​ልን?


በማ​ለዳ መገ​ሥ​ገ​ሣ​ች​ሁም ከንቱ ነው። ለወ​ዳ​ጆቹ እን​ቅ​ል​ፍን በሰጠ ጊዜ፥ እና​ንተ የመ​ከ​ራን እን​ጀራ የም​ት​በሉ፥ ከተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​በት ተነሡ።


ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ሌሊ​ትን ያስ​ገ​ዛ​ቸው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


አንቺ ወራዳ የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበ​ቀ​ል​ሽን የሚ​በ​ቀ​ልሽ ብፁዕ ነው።


ፀሐ​ይና ጨረቃ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ከዋ​ክ​ብ​ትና ብር​ሃን ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።


በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ናል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ም​ላ​ካ​ችን ስም ከፍ ከፍ እን​ላ​ለን፤ ልመ​ና​ህን ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ጽ​ም​ልህ።


ለም​ነኝ፥ አሕ​ዛ​ብን ለር​ስ​ትህ የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ፥ ለግ​ዛ​ትህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


መባ​ዬን ይዤ ወደ ቤትህ እገ​ባ​ለሁ፤


አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥ አሕ​ዛብ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል። አሕ​ዛብ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ሐሤ​ትም ያደ​ር​ጋሉ።


የዘ​መ​ኖ​ቻ​ች​ንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ነው፥ ቢበ​ዛም ሰማ​ንያ ዓመት ነው፤ ከእ​ነ​ዚህ ቢበዛ ግን ድካ​ምና መከራ ነው፤ የዋ​ህ​ነት ከእኛ አል​ፋ​ለ​ችና፥ እኛም ተገ​ሥ​ጸ​ና​ልና።


ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏ​ፏቴ ውስጥ በኀ​ይል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮ​ኻሉ፤ ያጠ​ፉ​ታ​ልም፤ እነ​ር​ሱም ከሩቅ ይወ​ር​ዳሉ፤ በተ​ራ​ራም ላይ እን​ዳለ እብቅ፥ በነ​ፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እን​ደ​ሚ​ያ​ዞ​ረው እንደ መን​ኰ​ራ​ኵር ትቢ​ያም ይበ​ተ​ናሉ።


ወደ ሰማይ አት​መ​ል​ከት፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕ​ዛብ ሁሉ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን፥ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንና የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት ሁሉ አይ​ተህ፥ ሰግ​ደ​ህ​ላ​ቸው፥ አም​ል​ከ​ሃ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​ስት ተጠ​ን​ቀቅ።


በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።