ልጨነቅ ቀርቤአለሁና፥ የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ።
ክፋት ቢያስቡብህ፣ ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤
ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ።
በአንተ ላይ ክፉ ነገር ለማድረግ ቢያቅዱና ቢያድሙም ምንም አይሳካላቸውም።
ኀጢአተኞች እነሆ፥ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖቹን በስውር ይነድፉ ዘንድ።
አሕዛብ ለምን ዶለቱ? ወገኖችስ ለምን ከንቱ ይናገራሉ?
በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ ብፁዓን ናቸው፤ ለዓለምና ለዘለዓለም ያመስግኑሃል።
እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ ከንቱን የሚያስቡ፥ በዚችም ከተማ ክፉን ምክር የሚመክሩ ሰዎች ናቸው።
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ “ሂዱ፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ” አላቸው።
ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስላዩት ፈሩአቸው።