የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 147:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቃሉን ለያ​ዕ​ቆብ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ይና​ገ​ራል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤ ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤ በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፥ ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱ ደመናን በሰማይ ላይ ይዘረጋል፤ ለምድር ዝናብን ይሰጣል፤ ተራራዎችንም በለምለም ሣር ይሸፍናል።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 147:8
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በም​ድር ላይ ደመ​ናን በጋ​ረ​ድሁ ጊዜ ቀስቴ በደ​መ​ናው ትታ​ያ​ለች፤


በም​ድር ላይ ዝና​ብን ይሰ​ጣል፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ውኃን ይል​ካል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።


ባድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ገ​ረ​ዝም፤ አይ​ኰ​ተ​ኰ​ትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵር​ን​ች​ትና እሾህ ይበ​ቅ​ል​በ​ታል፤ ዝና​ብ​ንም እን​ዳ​ያ​ዘ​ን​ቡ​በት ደመ​ና​ዎ​ችን አዝ​ዛ​ለሁ።


በውኑ በአ​ሕ​ዛብ ጣዖ​ታት መካ​ከል ያዘ​ንብ ዘንድ የሚ​ችል ይገ​ኛ​ልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ሊሰ​ጥና ሊያ​ጠ​ግብ ይች​ላ​ልን? አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ አን​ተን በተ​ስፋ እን​ጠ​ባ​በ​ቃ​ለን።


እና​ንተ የጽ​ዮን ልጆች ሆይ! በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጉ፤ ምግ​ብን በጽ​ድቅ ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ቀድ​ሞ​ውም የበ​ል​ጉ​ንና የመ​ከ​ሩን ዝናብ ያዘ​ን​ብ​ላ​ች​ኋ​ልና።


ከዚ​ህም ሁሉ ጋር መል​ካም ሥራን እየ​ሠራ ከሰ​ማይ ዝና​ምን፥ ፍሬ የሚ​ሆ​ን​በ​ት​ንም ወራት ሲሰ​ጠን፥ ልባ​ች​ን​ንም በመ​ብ​ልና በደ​ስታ ሲሞ​ላው ራሱን ያለ ምስ​ክር አል​ተ​ወም።”