እግዚአብሔር በመንገድህ ሁሉ ይኖራልና፥ እግሮችህም እንዳይነዋወጡ ያቆማቸዋልና።
እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና፤ እግርህንም በወጥመድ ከመያዝ ይጠብቃል።
ጌታ መታመኛህ ይሆናልና፥ እግርህም እንዳይጠመድ ይጠብቅሃልና።
እግዚአብሔር መታመኛህ ሆኖ በወጥመድም ከመያዝ ይጠብቅሃል።
ጥንቱን ፍርሀትህ፥ ተስፋህም፥ የመንገድህም ጠማማነት፥ ስንፍና አይደለምን?
ኢየሩሳሌምስ እንደ ከተማ የታነጸች ናት።
ዐሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።
እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጽኑዕ ተስፋ አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያን ይተዋል።
ለሚጸልይ ጸሎቱን ይሰጠዋል፤ የጻድቃንን ዘመን ይባርካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይደለምና።