የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ምሳሌ 20:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጹሕ ልብ አለኝ ብሎ የሚመካ ማን ነው? ከኀጢአትስ ንጹሕ ሆኖ የሚታይ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለመሆኑ፣ “ልቤን በንጽሕና ጠብቄአለሁ፤ ንጹሕ ነኝ፤ ኀጢአት የለብኝም” የሚል ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልቤን አነጻሁ፥ ከኃጢአትም ጠራሁ የሚል ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ኅሊናዬ ንጹሕ ነው፤ ኃጢአትም የለብኝም” ማለት የሚችል ሰው ይኖራልን?

ምዕራፉን ተመልከት



ምሳሌ 20:9
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“የማ​ይ​በ​ድ​ልም ሰው የለ​ምና አን​ተን ቢበ​ድሉ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ህም ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ብት​ሰ​ጣ​ቸው፥ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ወደ ጠላ​ቶች ሀገር ቢማ​ረ​ኩም፥


“የማ​ይ​በ​ድል ሰው የለ​ምና አን​ተን ቢበ​ድሉ፥ ብት​ቈ​ጣ​ቸ​ውም፥ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አሳ​ል​ፈህ ብት​ሰ​ጣ​ቸው፥ ሩቅም ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ሀገር ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው ቢማ​ር​ኩ​አ​ቸው፥


ከር​ኵ​ሰት የሚ​ነጻ ማን ነው? አንድ ስንኳ የለም።


ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሟች ሰው ማን ነው? ጻድ​ቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተ​ወ​ለደ ማን ነው?


ጻድቅ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ንጹሕ ይሆ​ናል? ከሴ​ትስ የተ​ወ​ለደ ራሱን ንጹሕ ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያፈ​ር​ስ​ሃል፤ ከቤ​ት​ህም ይነ​ቅ​ል​ሃል፥ ያፈ​ል​ስ​ሃ​ልም፥ ሥር​ህ​ንም ከሕ​ያ​ዋን ምድር።


በም​ድር ላይም መል​ካ​ምን የሚ​ሠራ ኀጢ​አ​ት​ንም የማ​ያ​ደ​ርግ ጻድቅ ሰው አይ​ገ​ኝ​ምና።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ከእ​ነ​ርሱ እን​በ​ል​ጣ​ለን? አይ​ደ​ለም፤ አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ንም፥ አረ​ማ​ዊ​ንም እነሆ፥ አስ​ቀ​ድ​መን ነቅ​ፈ​ና​ቸ​ዋል፤ ሁሉም ስተ​ዋ​ልና።


የሚ​ያ​ጠ​ራ​ጥ​ረ​ኝና ትዝ የሚ​ለኝ ነገር የለም፤ በዚ​ህም ራሴን አላ​መ​ጻ​ድ​ቅም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ረ​ም​ረ​ኛ​ልና።


ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።