አውስጢድ በሚባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹሕና ጻድቅ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።
ምሳሌ 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደጋግ ሰዎች በምድር ላይ ይቀመጣሉ፥ ጻድቃንም በእርስዋ ይኖራሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅኖች በምድሪቱ ይቀመጣሉና፤ ነቀፋ የሌለባቸውም በርሷ ላይ ጸንተው ይኖራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅኖች በምድር ላይ ይቀመጣሉና፥ ፍጹማንም በእርሷ ይኖራሉና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህች ምድር መኖር የሚችሉት ልበ ቅኖችና ደጋግ ሰዎች ናቸው። |
አውስጢድ በሚባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹሕና ጻድቅ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።
እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ፤ መንጋዎቹም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድስት ሺህም ግመሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩ።