ትምክሕት የአስተዋይ ሰው ልቡናን ያሳዝነዋል፥ አላዋቂ ግን ተገርፎ ግርፋቱ አይታወቀውም፥
መቶ ግርፋት ሞኝን ከሚሰማው ይልቅ፣ ተግሣጽ ለአስተዋይ ጠልቆ ይሰማል።
መቶ ግርፋት በሰነፍ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሣጽ በአስተዋይ ሰው ጠልቆ ወደ ልቡ ይገባል።
ሞኝ መቶ ጊዜ ተገርፎ ከሚማረው ይልቅ አስተዋይ ሰው ከአንድ ጊዜ በማይበልጥ ተግሣጽ የሚማረው ይበልጣል።
አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦ “አንተ ተስፋዬ ነህ፥ በሕያዋንም ምድር አንተ ዕድል ፋንታዬ ነህ” አልሁ።
ዐዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፤ የማይሰማ ልጅ ግን ይጠፋል።
አላዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሥጽ ያቃልላል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ዐዋቂ ነው። እውነት ከበዛ ዘንድ ብዙ ኀይል አለ፥ ኀጢአተኞች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፥
ክፉ ሰው ሁሉ ጠብን ያነሣሣል፤ እግዚአብሔርም ምሕረት የሌለውን መልአክ ይልክበታል።
በደሉን የሚሰውር ሰው ዕርቅን ይሻል፤ በደሉን መሰወር የሚጠላ ግን ቤተሰቦችንና ወዳጆችን ይለያያል።
ፌዘኛን ብትገርፈው አላዋቂው ብልሃተኛ ይሆናል፤ አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው ግን ዕውቀትን ያገኛል።
እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።