የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ፊልጵስዩስ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኤዎ​ድ​ያና ስን​ጣ​ክን ሆይ፥ በአ​ንድ ልብ ጌታ​ች​ንን ለማ​ገ​ል​ገል ታስቡ ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በጌታ አንድ ሐሳብ እንዲኖራቸው ኤዎድያንን እለምናለሁ፤ ሲንጤኪንንም እለምናለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በአንድ አሳብ በጌታ እንዲስማሙ ኤዎድያንን እመክራለሁ፤ ሲንጤኪንንም እመክራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኤዎድያና ሲንጢኪ እርስ በርሳቸው በጌታ ተስማምተው እንዲኖሩ እለምናቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በአንድ አሳብ በጌታ እንዲስማሙ ኤዎድያንን እመክራለሁ ሲንጤኪንንም እመክራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ፊልጵስዩስ 4:2
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በመ​ን​ገድ እርስ በር​ሳ​ችሁ አት​ጣሉ።”


ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! አንድ ቃል እን​ድ​ት​ና​ገሩ፥ እን​ዳ​ታ​ዝኑ፥ ፍጹ​ማ​ንም እን​ድ​ት​ሆኑ፥ ሁላ​ች​ሁ​ንም፦ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ት​ለ​ያ​ዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆና​ችሁ ኑሩ።


ነገር ግን በደ​ረ​ስ​ን​በት ሥራ በአ​ን​ድ​ነት እን​በ​ርታ።


ከሁሉ ጋር ወደ ሰላም ሩጡ፤ ቅድ​ስ​ና​ች​ሁ​ንም አት​ተዉ፤ ያለ እርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​የው የለም።