የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 36:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዮ​ሴፍ ልጆች ወገ​ኖች የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጅ የገ​ለ​ዓድ ልጆች ወገን አለ​ቆች መጡ፤ በሙ​ሴና በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛር፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አባ​ቶች አለ​ቆች ፊት ተና​ገሩ፤ አሉም፦

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዮሴፍ ዝርያ ጐሣዎች የሆኑ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ጐሣ የቤተ ሰብ አለቆች ወደ ሙሴና የእስራኤላውያን ቤተ ሰቦች አለቆች ወደሆኑት መሪዎች ቀርበው ተናገሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዮሴፍ ልጆች ወገኖች የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ወገን አለቆች ቀረቡ፥ በሙሴና በእስራኤልም ልጆች አባቶች አለቆች ፊት ተናገሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የዮሴፍ ልጅ ምናሴ የወለደው የማኪር ልጅ የገለዓድ ጐሣ የሆኑት የቤተሰብ አለቆች ወደ ሙሴና ወደ ሌሎቹም የእስራኤል ሕዝብ አለቆች ቀርበው እንዲህ አሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከዮሴፍ ልጆች ወገኖች የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ወገን አለቆች ቀረቡ፥ በሙሴና በእስራኤልም ልጆች አባቶች አለቆች ፊት ተናገሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 36:1
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም የኤ​ፍ​ሬ​ምን ልጆች እስከ ሦስት ትው​ልድ አየ። የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጆ​ችም በዮ​ሴፍ ጭን ላይ ተወ​ለዱ።


ከዮ​ሴፍ ልጅ ከም​ናሴ ወገን ፥ የም​ናሴ ልጅ፥ የማ​ኪር ልጅ፥ የገ​ለ​አድ ልጅ፥ የኦ​ፌር ልጅ፥ የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች መጡ፤ የእ​ነ​ዚ​ህም ሴቶች ልጆች ስሞች መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ።


በም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በሙ​ሴና በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛር፥ በአ​ለ​ቆ​ቹም፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ ፊት ቆመው እን​ዲህ አሉ፦


“የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ልጆች እው​ነት ተና​ግ​ረ​ዋል፤ በአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች መካ​ከል የር​ስት ድርሻ ስጣ​ቸው፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ርስት ለእ​ነ​ርሱ ስጥ።