የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 32:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ሻ​ገሩ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ ለምን ታጣ​ም​ማ​ላ​ችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤላውያን ተሻግረው እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ ተስፋ የምታስቈርጧቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ወደሚሰጣቸው ምድር እንዳይሻገሩ የእስራኤልን ልጆች ልብ ለምን ታደክማላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእስራኤል ሕዝብ ዮርዳኖስን ተሻግረው እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ ተስፋ የምታስቈርጡት ለምንድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር ወደሚሰጣቸው ምድር እንዳይሻገሩ የእስራኤልን ልጆች ልብ ለምን ታደክማላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 32:7
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩት፥ “ወደ ላክ​ኸን ምድር ደረ​ስን፤ እር​ስ​ዋም ወተ​ትና ማር ታፈ​ስ​ሳ​ለች፤ ፍሬ​ዋም ይህ ነው።


ከእ​ርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን ፥ “በኀ​ይል ከእኛ ይበ​ረ​ታ​ሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መው​ጣት አን​ች​ልም” አሉ።


ስማ​ቸ​ውም ይህ ነበረ፤ ከሮ​ቤል ነገድ የዝ​ኩር ልጅ ሰሙ​ኤል፤


ከሖ​ርም ተራራ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ተጓዙ፤ የኤ​ዶ​ም​ንም ምድር ዞሩ​አት፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ገድ ተበ​ሳጩ።


ሙሴም ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ወደ ጦር​ነት ሲሄዱ እና​ንተ በዚህ ትቀ​መ​ጣ​ላ​ች​ሁን?


ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አዩ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሰጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ገቡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ መለሱ።


ጳው​ሎስ ግን መልሶ፥ “ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እያ​ለ​ቀ​ሳ​ችሁ ልቤን ትሰ​ብ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ እኮ ተስፋ የማ​ደ​ር​ገው መከ​ራ​ንና እግር ብረ​ትን ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሞ​ትም ቢሆን የቈ​ረ​ጥሁ ነኝ” አለ።


ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’