ዘኍል 32:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴም ልጅ የማኪር ልጅ ወደ ገለዓድ ሄዶ ገለዓድን ያዘ፤ በእርስዋም የነበሩትን አሞሬዎናውያንን አጠፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናሴ ልጅ የሆነው የማኪር ዘሮች ወደ ገለዓድ ሄደው ምድሪቱን በመያዝ፣ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አሳደዷቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምናሴም ልጅ የማኪር ልጆች ወደ ገለዓድ ሄዱ፥ ያዝዋትም፥ በእርሷም የነበሩትን አሞራውያንን አሳደዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምናሴ ልጅ የማኪር ቤተሰብ የገለዓድን ምድር በመውረር ወረሰ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንን አባረረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናሴም ልጅ የማኪር ልጆች ወደ ገለዓድ ሄዱ፥ ወሰዱአትም፥ በእርስዋም የነበሩትን አሞራውያንን አሳደዱ። |
የምናሴ ልጆች ነገድ ድንበር ይህ ነው፤ የዮሴፍ በኵር እርሱ ነውና። የምናሴም በኵር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ።
በዚያም ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፤ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞሬዎናውያን ሀገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት አስጨነቁአቸው።
በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ! በሕዝብ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፤ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።