ዘኍል 32:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናምራን፥ ቤታራንን ሰባት የተመሸጉ ከተሞች አድርገው ሠሩ፤ አስረዘሙአቸውም፤ የበጎች በረቶችንም ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤትኒምራንና ቤትሃራንን የተመሸጉ ከተሞች አድርገው ሠሯቸው፤ እንዲሁም ለበግና ለፍየል መንጎቻቸው ጕረኖዎች አበጁላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤትነምራን፥ ቤትሃራንን የተመሸጉ ከተሞች አድርገው ሠሩ፤ የበጎች በረቶችንም ሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤትኒምራንና የቤትሃራንን ከተሞች በማደስ ለከብቶቹም በረቶችን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤትነምራን፥ ቤትሃራንን የተመሸጉ ከተሞች አድርገው ሠሩ፤ የበጎች በረቶችንም ሠሩ። |
በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትንምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኬኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበረ።