የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እንደ ድን​ኳኑ ሥራ​ዎች ሁሉ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ዕቃና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ ይጠ​ብቁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የማደሪያውን ሥራ በመሥራትና የእስራኤላውያንን ግዴታ በመወጣት የመገናኛውን ድንኳን ሁሉ ይጠብቁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የማደሪያውንም ሥራ እየሠሩ፥ የመገናኛውን ድንኳን ዕቃ ሁሉ ይጠብቃሉ፥ ለእስራኤልንም ልጆች ያለባቸውን ግዴታ ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚገኙ መገልገያ ዕቃዎች ኀላፊዎች ይሆናሉ። እስራኤላውያንንም በድንኳኑ ውስጥ በማገልገል ተግባራቸውን ይፈጽማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የማደሪያውንም ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የመገናኛውን ድንኳን ዕቃ ሁሉ ይጠብቁ፥ የእስራኤልን ልጆች ለማገልገል የሚያስፈልገውንም ነገር ይጠብቁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 3:8
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ጨ​ረ​ሻ​ውም በዳ​ዊት ትእ​ዛዝ ከሃያ አም​ስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት የሌዊ ልጆች ተቈ​ጠሩ።


አሁ​ንም በፊቱ ትቆ​ሙና ታገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥ​ኑ​ለ​ትም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​አ​ች​ኋ​ልና ቸል አት​በሉ።”


እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕቃ የም​ት​ሸ​ከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩ​ስን ነገር አት​ንኩ፤ ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ ራሳ​ች​ሁን ለዩ።


ድን​ኳ​ኑም ተነ​ቀለ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም የተ​ሸ​ከሙ የጌ​ድ​ሶን ልጆ​ችና የሜ​ራሪ ልጆች ተጓዙ።


የቀ​ዓ​ትም ልጆች ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን ተሸ​ክ​መው ተጓዙ፤ እነ​ዚ​ህም እስ​ኪ​መጡ ድረስ እነ​ዚያ ድን​ኳ​ኑን ተከሉ።


የድ​ን​ኳ​ኑን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሕጉ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ይጠ​ብቁ።


ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ አሮ​ንና ወደ ልጆቹ ወደ ካህ​ናቱ ታገ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ። ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተለ​ይ​ተው ለእኔ ሀብት ሆነው ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ድርሻ እኩ​ሌታ፥ ከሰ​ዎ​ችም፥ ከበ​ሬ​ዎ​ችም፥ ከበ​ጎ​ችም፥ ከአ​ህ​ዮ​ችም፥ ከእ​ን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ ከአ​ምሳ አንድ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ድን​ኳን ሥር​ዐት ለሚ​ጠ​ብቁ ለሌ​ዋ​ው​ያን ትሰ​ጣ​ለህ።”


አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


የጌ​ድ​ሶን ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ባለው ሥራ​ቸው ሁሉ የሜ​ራሪ ልጆች ወገ​ኖች አገ​ል​ግ​ሎት ይህ ነው፤ እነ​ር​ሱም ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።”