የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“የሌ​ዊን ነገድ አቅ​ር​በህ ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ በካ​ህኑ በአ​ሮን ፊት አቁ​ማ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“የሌዊን ነገድ አምጥተህ ካህኑን አሮንን በአገልግሎቱ እንዲረዱት ከፊቱ አቁማቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“የሌዊን ነገድ አምጥተህ አቅርብ እንዲያገለግሉትም በካህኑ በአሮን ፊት አቁማቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የሌዊን ነገድ አቅርበህ ለካህኑ አሮን አገልጋዮች እንዲሆኑ መድባቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሌዊን ነገድ አቅርበህ ያገለግሉት ዘንድ በካህኑ በአሮን ፊት አቁማቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 3:6
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያን ጊዜም ዳዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይሸ​ከሙ ዘንድ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ረ​ጣ​ቸው ከሌ​ዋ​ው​ያን በቀር ማንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይሸ​ከም ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም” አለ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩና በየ​መ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል፥ ቅዱ​ሱ​ንም ዕቃ ሁሉ ለማ​ን​ጻት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ለመ​ሥ​ራት ከአ​ሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥር​ዐት፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን የአ​ሮ​ንን ልጆች ሥር​ዐት ለመ​ጠ​በቅ ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹና ልጆቹ እነ​ዚህ ነበሩ፤ ከቀ​ዓት ልጆች ዘማ​ሪው ኤማን ነበረ፤ እር​ሱም የኢ​ዩ​ኤል ልጅ፥ የሳ​ሙ​ኤል ልጅ፤


አሁ​ንም በፊቱ ትቆ​ሙና ታገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥ​ኑ​ለ​ትም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​አ​ች​ኋ​ልና ቸል አት​በሉ።”


በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ካህ​ና​ቱን በየ​ማ​ዕ​ር​ጋ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አቆሙ።


ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ይሆን ዘንድ ይህን ትእዛዝ እንደ ሰደድሁላችሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“ለሌ​ዊም ልጆች እነሆ፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ስለ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዐሥ​ራት ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ።


“ከዚ​ያም በኋላ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን፥ በሰ​ፈ​ሮ​ቹም መካ​ከል የሌ​ዋ​ው​ያን ወገን ይጓ​ዛል፤ እንደ አሰ​ፋ​ፈ​ራ​ቸው ሰው ሁሉ በየ​ስ​ፍ​ራው፥ በየ​ዓ​ላ​ማ​ውም ይጓ​ዛሉ።


ሌዋ​ው​ያን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


በዚ​ያን ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸ​ከም ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስ​ሙም ይባ​ርክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌ​ዊን ነገድ ለየ።