ዘኍል 20:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘ አደረገ፤ በማኅበሩም ሁሉ ፊት እያዩ ወደ ሖር ተራራ አወጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ መላው ማኅበረ ሰብ እያያቸው ወደ ሖር ተራራ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ጌታ እንዳዘዘ አደረገ፤ ማኅበሩም ሁሉ እያዩ ወደ ሖር ተራራ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፤ መላው ማኅበር እየተመለከታቸው ወደ ሖር ተራራ ወጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘ አደረገ፤ ማኅበሩም ሁሉ እያዩ ወደ ሖር ተራራ ወጡ። |
ሙሴም የአሮንን ልብስ አወጣ፤ ልጁንም አልዓዛርን አለበሰው፤ አሮንም በዚያ በተራራው ራስ ላይ ሞተ፤ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ራስ ላይ ወረዱ።