እንዲሁም ካህኑ ኬልቅያስና አኪቃም ዓክቦርም ሳፋንና ዓሳያም ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢዪቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እርስዋም በዚያ በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር፤ ለእርስዋም ነገሩአት።
ነህምያ 7:72 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀሩትም ሕዝብ የሰጡት ሃያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባትም የካህናት ልብስ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀረው ሕዝብ በአጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,000 ምናን ብርና 67 ልብሰ ተክህኖ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ በር ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡ አንዳንዶቹ፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና እስራኤልም ሁሉ በገዛ ከተሞቻቸው ተቀመጡ፥ ሰባተኛውም ወር መጣ የእስራኤል ልጆችም በገዛ ከተሞቻቸው ተቀምጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀሩትም ሕዝብ የሰጡት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባትም የካህናት ልብስ ነበረ። |
እንዲሁም ካህኑ ኬልቅያስና አኪቃም ዓክቦርም ሳፋንና ዓሳያም ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢዪቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እርስዋም በዚያ በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር፤ ለእርስዋም ነገሩአት።
ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ፥ የእስራኤልም ልጆች በከተሞቻቸው ሳሉ፥ ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።
የቀሩትም ሕዝብ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በረኞቹም፥ መዘምራንም፥ ናታኒምም፥ ከምድርም አሕዛብ ራሳቸውን የለዩና ወደ እግዚአብሔር ሕግ የገቡ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉትም ሁሉ ወንድሞቻቸውንና ታላላቆቻቸውን አበረታቱ፤
ከአባቶች ቤቶች አለቆችም ዐያሌዎቹ በሥራው ቤተ መዛግብት ውስጥ ሃያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ።
ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም፥ ከሕዝቡም ዐያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።