የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ነህምያ 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በደ​ላ​ቸ​ው​ንም አት​ክ​ደን፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከፊ​ትህ አይ​ደ​ም​ሰስ፤ በሠ​ራ​ተ​ኞች ፊት አስ​ቈ​ጥ​ተ​ው​ሃ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የፈረሰውን በሚሠሩት ፊት የስድብ ናዳ አውርደዋልና በደላቸውን ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አታጥፋው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጠላቶቻችንም፦ “በመካከላቸው እስክንገባና እስክንገድላቸው ድረስ፥ ሥራቸውንም እስክናስተጓጉል ድረስ አያውቁም፥ አያዩምም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር ምሕረት አታድርግላቸው፤ የፈረሰውን በመሥራታችን በስድብ አዋርደውናልና በደላቸውን አትርሳ።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በደላቸውንም አትክደን፥ ኃጢአታቸውም ከፊትህ አይደምሰስ፥ በሠራተኞች ፊት አስቆጥተውሃልና።

ምዕራፉን ተመልከት



ነህምያ 4:5
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደክ​ሞና እጁ ዝሎ ሳለ እወ​ድ​ቅ​በ​ታ​ለሁ፤ አስ​ፈ​ራ​ው​ማ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸ​ሻል፤ ንጉ​ሡ​ንም ብቻ​ውን እገ​ድ​ለ​ዋ​ለሁ፤


ቅጥ​ሩ​ንም ሠራን፤ ቅጥ​ሩም ሁሉ እስከ እኩ​ሌ​ታው ድረስ ተጋ​ጠመ፤ ሕዝቡ ከልብ ይሠራ ነበ​ርና።


ኀያል ሆይ፥ በክ​ፋት ለምን ትኰ​ራ​ለህ? ሁል​ጊ​ዜስ ለምን ትበ​ድ​ላ​ለህ?


አድ​ር​ገ​ህ​ል​ኛ​ልና ለዘ​ለ​ዓ​ለም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ በጻ​ድ​ቃ​ን​ህም ዘንድ መል​ካም ነውና ምሕ​ረ​ት​ህን ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ታና​ሹም ሰው ዝቅ ብሎ​አል፤ ታላ​ቁም ሰው ተዋ​ር​ዶ​አል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።


መተ​ላ​ለ​ፍን፦ ስለ እኔ ስለ ራሴ ስል የም​ደ​መ​ስስ እኔ ነኝ፤ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አላ​ስ​ብም።


መተ​ላ​ለ​ፍ​ህን እንደ ደመና፥ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም እንደ ጭጋግ ደም​ስ​ሼ​አ​ለሁ፤ ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና ወደ እኔ ተመ​ለስ።


አንተ ግን አቤቱ! ይገ​ድ​ሉኝ ዘንድ በላዬ የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ሁሉ ታው​ቃ​ለህ፤ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ይቅር አት​በል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ከፊ​ትህ አት​ደ​ም​ስስ፤ በፊ​ት​ህም ይው​ደቁ፤ በቍ​ጣህ ጊዜ እን​ዲሁ አድ​ር​ግ​ባ​ቸው።”


ታው። ልቅ​ሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክ​ሞ​አ​ልና፥ ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድ​ረስ፥ ስለ ኀጢ​አቴ ሁሉ እኔን እንደ ቃረ​ም​ኸኝ እነ​ር​ሱን ቃር​ማ​ቸው።


የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል።