የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ነህምያ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ገባ​ዖ​ና​ዊው መል​ጥ​ያና ሜሮ​ና​ታ​ዊው ያዴን፥ እስከ ወን​ዙም ማዶ አለቃ ግዛት የሆኑ የገ​ባ​ዖ​ንና የመ​ሴፋ ሰዎች ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእነርሱም ቀጥሎ የዕድሳቱ ሥራ የተከናወነው በኤፍራጥስ ማዶ በሚገኘው አገረ ገዥ ሥልጣን ሥር ባሉት በገባዖንና በምጽጳ ሰዎች በገባዖናዊው በመልጥያና በሜሮኖታዊው በያዶን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በአጠገባቸውም ጊብዖናዊው ሜላጥያ፥ ሜሮኖታዊው ያዶንና ከወንዙ ማዶ ያለው ገዢ ሥር የሆኑት የጊብዖንና የሚጽጳ ሰዎች አደሱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የገባዖን ተወላጅ የሆነው መላጥያ፥ የሜሮኖት ተወላጅ የሆነው ያዶንና የገባዖንና የምጽጳ ሰዎች የኤፍራጥስ ምዕራብ አገረ ገዢ እስከሚኖርበት ቤት ድረስ ያለውን ክፍል ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በአጠገባቸውም ገባዖናዊው መልጥያና ሜሮኖታዊው ያዶን፥ የወንዙም ማዶ አለቃ ግዛት የሆኑት የገባዖንና የምጽጳ ሰዎች አደሱ።

ምዕራፉን ተመልከት



ነህምያ 3:7
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሡ ዳዊ​ትም የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች ጠራ፤ የገ​ባ​ዖን ሰዎ​ችም ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን የተ​ረፉ ነበሩ እንጂ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወገን አል​ነ​በ​ሩም፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ምለ​ው​ላ​ቸው ነበር፤ ሳኦል ግን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና ለይ​ሁዳ ስለ ቀና ሊገ​ድ​ላ​ቸው ወድዶ ነበር።


በግ​መ​ሎ​ቹም ላይ እስ​ማ​ኤ​ላ​ዊው ኤቢ​ያስ ሹም ነበረ፤ በአ​ህ​ዮ​ቹም ላይ ሜሮ​ኖ​ታ​ዊው ኢያ​ድስ ሹም ነበረ፤


የይ​ሁዳ ንጉሥ አሳም የይ​ሁ​ዳን ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ባኦስ ይሠ​ራ​በት የነ​በ​ረ​ውን የራ​ማን ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወሰደ፤ እር​ሱም ገባ​ዖ​ን​ንና መሴ​ፋን ሠራ​በት።


ለን​ጉሡ ለአ​ር​ተ​ሰ​ስታ የላ​ኩት የደ​ብ​ዳቤ ቃልም ይህ ነው፥ “በወ​ንዝ ማዶ ያሉት ሰዎች ባሪ​ያ​ዎ​ችህ፤


በአ​ጠ​ገ​ቡም የመ​ሴፋ ገዢ የኢ​ያሱ ልጅ አዙር በማ​ዕ​ዘኑ አጠ​ገብ በመ​ወ​ጣ​ጫው ግንብ አን​ጻር ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።