የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ነህምያ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አቤቱ የሰ​ማይ አም​ላክ ሆይ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ህና ትእ​ዛ​ዝ​ህን ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥ ታላ​ቅና የተ​ፈ​ራህ አም​ላክ ሆይ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም እንዲህ አልሁ፤ “ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያከብሩ የፍቅርህን ቃል ኪዳን የምትጠብቅ ታላቅና የተፈራህ አምላክ፣ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም አልሁ፦ ታላቅና የተፈራ አምላክ፥ ለሚወድዱትና ትእዛዙን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የሚጠብቅ፥ የሰማይ አምላክ ጌታ ሆይ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እግዚአብሔር የሰማይ አምላክ ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ እኛም በፍርሃት በፊትህ እንቆማለን፤ አንተ ከሚወዱህና ትእዛዞችህንም ከሚጠብቁ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳንህን ትጠብቃለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም አልሁ፦ “አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ነህምያ 1:5
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! በላይ በሰ​ማይ፥ በታ​ችም በም​ድር አን​ተን የሚ​መ​ስል አም​ላክ የለም፤ በፍ​ጹም ልቡ በፊ​ትህ ለሚ​ሄድ ባሪ​ያህ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥


አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ካወ​ጣ​ኸው ከሕ​ዝ​ብህ ፊት አሕ​ዛ​ብን በማ​ሳ​ደድ ታላ​ቅና የከ​በረ ስምን ለአ​ንተ ታደ​ርግ ዘንድ፥ ለአ​ን​ተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደ መራ​ኸው እንደ አንተ ሕዝብ እንደ እስ​ራ​ኤል ያለ በም​ድር ላይ ሌላ ሕዝብ የለም።


“የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ በይ​ሁ​ዳም ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ እን​ዳ​ስብ አደ​ረ​ገኝ፤


ንጉ​ሡም፥ “ምን ትለ​ም​ነ​ኛ​ለህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አም​ላክ ጸለ​ይሁ።


አይ​ችም ተነ​ሣሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹ​ንም፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ፥ “አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ ታላ​ቁ​ንና የተ​ፈ​ራ​ውን አም​ላ​ካ​ች​ንን አስቡ፤ ስለ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ቤቶ​ቻ​ች​ሁም ተዋጉ” አል​ኋ​ቸው።


መጥ​ተ​ውም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይወ​ጉና ያፈ​ር​ሷት ዘንድ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ።


“አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ ታላ​ቅና ኀያል ጽኑ​ዕና የተ​ፈ​ራ​ኸው አም​ላክ ሆይ፥ ከአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ በእ​ኛና በነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን፥ በአ​ለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ በካ​ህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በሕ​ዝ​ብህ ሁሉ ላይ የደ​ረ​ሰው መከራ ሁሉ በፊ​ትህ ጥቂት መስሎ አይ​ታ​ይህ።


ለም​ድር ሁሉ ደስ​ታን የሚ​ያ​ዝዝ፥ የጽ​ዮን ተራ​ራ​ዎች በመ​ስዕ በኩል ናቸው። የታ​ላቁ ንጉሥ ከተማ ናት።


ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምስ ምሕ​ረ​ቱን ለልጅ ልጅ ይቈ​ር​ጣ​ልን?


ተራ​ሮች ሳይ​ወ​ለዱ፥ ምድ​ርም ዓለ​ምም ሳይ​ሠሩ፥ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ።


ሰውን ወደ ኀሣር አት​መ​ል​ሰው፤ የሰው ልጆች ሆይ፥ ተመ​ለሱ ትላ​ለህ፤


ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በፊ​ትህ አስ​ቀ​መ​ጥህ፥ ዓለ​ማ​ች​ንም በፊ​ትህ ብር​ሃን ነው።


ለሚ​ወ​ድ​ዱኝ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ ምሕ​ረ​ትን የማ​ደ​ርግ አም​ላክ ነኝና።


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ይህ​ችን ፍርድ ሰም​ታ​ችሁ ብት​ጠ​ብ​ቋት፥ ብታ​ደ​ር​ጓ​ትም፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳ​ንና ምሕ​ረት ለእ​ና​ንተ ይጠ​ብ​ቅ​ላ​ች​ኋል፤


ከፊ​ታ​ቸው አት​ደ​ን​ግጥ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከአ​ንተ ጋር ነውና፥ እር​ሱም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅና ጽኑዕ ነውና።


አን​ተም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ትም፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ ቃል ኪዳ​ኑ​ንና ምሕ​ረ​ቱን እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ የሚ​ጠ​ብቅ የታ​መነ አም​ላክ እንደ ሆነ ዕወቅ፤