የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ናሆም 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍም ይንቦገቦጋል፥ ጦርም ይብለጨለጫል፣ የተገደሉትም ይበዛሉ፥ በድኖችም በክምር ይከመራሉ፥ ሬሳቸውም አይቈጠርም፣ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፈረሰኛው ይጋልባል፤ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፤ ጦር ያብረቀርቃል። የሞተው ብዙ ነው፤ ሬሳ በሬሳ ሆኗል፤ ስፍር ቍጥር የለውም፤ መተላለፊያ አልተገኘም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፥ ጦር ይብለጨለጫል የተገደለ ብዛት፥ የበድን ክምር፥ ሬሳው ማለቂያ የለውም፤ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፈረሰኞች ወደፊት እየገፉ የሚያብረቀርቅ ሰይፋቸውንና የሚያብለጨልጭ ጦራቸውን ያነሣሉ፤ ብዙ ሰዎች ስለ ተገደሉ ሬሳዎች ተከምረዋል፤ ከሬሳውም ብዛት የተነሣ በዚያ የሚያልፍ ሰው ሁሉ ይደናቀፋል።

ምዕራፉን ተመልከት



ናሆም 3:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አዳ​ም​ንም አስ​ወ​ጣው፤ ደስታ በሚ​ገ​ኝ​ባት በገ​ነት አን​ጻ​ርም አኖ​ረው፤ ወደ ሕይ​ወት ዛፍ የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም መን​ገድ ለመ​ጠ​በቅ የም​ት​ገ​ለ​ባ​በጥ የነ​በ​ል​ባል ሰይ​ፍን በእ​ጃ​ቸው የያዙ ኪሩ​ቤ​ልን አዘ​ዛ​ቸው።


በዚ​ያ​ችም ሌሊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ መጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድ​ኖች ነበሩ።


ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ገ​ደ​ሉት በድ​ና​ቸው ይጣ​ላል፤ የሬ​ሳ​ቸ​ውም ግማት ይሸ​ታል፤ ተራ​ሮ​ቹም ከደ​ማ​ቸው የተ​ነሣ ይር​ሳሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድ​ኖች ሆነው አገ​ኙ​አ​ቸው።


ምድ​ርም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሳት ሰውም ሁሉ በሰ​ይፉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተቀ​ሥ​ፈው የሞ​ቱት ይበ​ዛሉ።


አን​ተና ጭፍ​ሮ​ችህ ሁሉ፥ ከአ​ን​ተም ጋር ያሉ ሕዝብ በም​ድረ በዳ ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለሚ​ና​ጠቁ ወፎች ሁሉና ለም​ድር አራ​ዊ​ትም መብል አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ቸው ከሰ​ይፍ እን​ዲ​ሸሹ እርስ በር​ሳ​ቸው ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላሉ፤ እና​ን​ተም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም።


ሰረገሎች በመንገድ ላይ ይነጕዳሉ፥ አደባባይም ይጋጫሉ፣ መልካቸው እንደ ፋና ነው፥ እንደ መብረቅም ይከንፋሉ።


ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሃን የተነሣ፥ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሣ፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ።