ማቴዎስ 9:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈሪሳውያን ግን “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈሪሳውያን ግን፣ “አጋንንትን የሚያወጣው፣ በአጋንንት አለቃ ነው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈሪሳውያን ግን “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈሪሳውያን ግን “እርሱ አጋንንትን የሚያስወጣው በአጋንንት አለቃ አማካይነት ነው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈሪሳውያን ግን፦ በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል አሉ። |
ነገር ግን ከመካከላቸው፥ “በአጋንንት አለቃ በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣቸዋል” ያሉ ነበሩ፤ እርሱም መልሶ፥ “ሰይጣን ሰይጣንን ማውጣት እንደምን ይቻለዋል?” አላቸው።