ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።
ስለዚህ በፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።
ስለዚህ በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ።
ስለዚህ፥ ሐሰተኞች ነቢያትን በሥራቸው ፍሬ ታውቁአቸዋላችሁ።
“ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፤ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ።
ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?
ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃል፤ ከእሾህ በለስን አይለቅሙም፤ ከደንደርም ወይንን አይለቅሙም።
አሁንም እላችኋለሁ፥ ከእነዚህ ሰዎች ራቁ፤ ተዉአቸውም፤ ይህ ምክራቸው፥ ይህም ሥራቸው ከሰው የተገኘ ከሆነ ያልፋል ይጠፋልም።
ወንድሞቼ ሆይ! በለስ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውሃም ጣፋጭ ውሃ አይወጣም።