የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ማርቆስ 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ድኾች ምን ጊዜም ከእናንተ ጋራ ናቸው፤ በፈለጋችሁ ጊዜ ልትረዷቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ አልኖርም፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ድኾች ምንም ጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ በፈለጋችሁ ጊዜ ልትረዷቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ድኾች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ስለ ሆኑ በፈለጋችሁ ጊዜ ልትረዱአቸው ትችላላችሁ፤ እኔን ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አታገኙኝም፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፥ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም።

ምዕራፉን ተመልከት



ማርቆስ 14:7
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤


ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ “ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች።


ልጆች ሆይ፥ ገና ጥቂት ጊዜ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ለአ​ይ​ሁ​ድም እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አይ​ቻ​ላ​ች​ሁም እን​ዳ​ል​ኋ​ቸው፥ አሁ​ንም ለእ​ና​ንተ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


ከአብ ወጣሁ፤ ወደ ዓለ​ምም መጣሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ዓለ​ምን እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ ወደ አብም እሄ​ዳ​ለሁ።”


አሁን ግን ወደ ላከኝ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ እንኳ፦ ‘ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?’ ብሎ አይ​ጠ​ይ​ቀ​ኝም።


እን​ግ​ዲህ በዓ​ለም አል​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ግን በዓ​ለም ይኖ​ራሉ፤ እኔም ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነ​ዚ​ህን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስ​ምህ ጠብ​ቃ​ቸው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከጥ​ንት ጀምሮ በቅ​ዱ​ሳን ነቢ​ያቱ አፍ እስከ ተና​ገ​ረው የመ​ደ​ራ​ጀት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀ​በ​ለው ዘንድ ይገ​ባል።


ድሃ ከም​ድ​ርህ ላይ አይ​ታ​ጣ​ምና ስለ​ዚህ እኔ፦ በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ላለው ድሃ፥ ለሚ​ለ​ም​ን​ህም ወን​ድ​ምህ እጅ​ህን ዘርጋ ብዬ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ።


የቅዱሳን ልብ በአንተ ሥራ ስለ ዐረፈ፥ ወንድሜ ሆይ! በፍቅርህ ብዙ ደስታንና መጽናናትን አግኝቼአለሁና።