ማታ ማታም ከከተማ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር።
በመሸም ጊዜ ከከተማዪቱ ወጥተው ሄዱ።
በመሸም ጊዜ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከከተማ ወጡ።
ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ፤ በዚያም አደረ።
ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ።
ቀን ቀን በመቅደስ ያስተምር ነበር፤ ሌሊት ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በሚባለው ተራራ ያድር ነበር።
የብርሃን ልጆች ትሆኑ ዘንድ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃን እመኑ” ጌታችን ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ሄደ፤ ተሰወራቸውም።