የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሚልክያስ 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ለእስራኤል ሁሉ ሕጎችና ሥርዐቶች ይሆኑ ዘንድ፣ ለአገልጋዬ ለሙሴ በኮሬብ የሰጠሁትን ሕግ አስቡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የአገልጋዬን የሙሴን ሕግ አስታውሱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይመሩበት ዘንድ በሲና ተራራ ላይ ለአገልጋዬ ለሙሴ የሰጠሁትን ሕግና ትእዛዝ አስታውሱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሚልክያስ 4:4
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ምስ​ጋ​ና​ውን ያጸ​ድ​ቅና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መከረ።


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በመ​ን​ገድ ላይ ቁሙ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ የቀ​ደ​መ​ች​ው​ንም መን​ገድ ጠይቁ፤ መል​ካ​ሚቱ መን​ገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ሂዱ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ሁም መድ​ኀ​ኒ​ትን ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤” እነ​ርሱ ግን፥ “አን​ሄ​ድ​ባ​ትም” አሉ።


እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ኦሪ​ትን እን​ሽ​ራ​ለን? አን​ሽ​ርም፤ ኦሪ​ትን እና​ጸ​ና​ለን እንጂ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ወደ እኔ ሰብ​ስ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ በም​ድር ላይ በሕ​ይ​ወት በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ እኔን መፍ​ራት ይማ​ሩና ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎ​ኛ​ልና በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ በፈ​ጣ​ሪ​ያ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ቆማ​ችሁ ንገ​ራ​ቸው።


ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን እን​ዳ​ት​ረሱ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የከ​ለ​ከ​ለ​ውን፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እን​ግ​ዲህ ተጠ​ን​ቀቁ።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳ​ኑን አጸና።


“ዛሬ እኔ አን​ተን የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ፍር​ዱን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ባለ​መ​ጠ​በቅ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ ተጠ​ን​ቀቅ፤


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ብት​ረሳ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተል፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥ ብት​ሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውም፥ ፈጽሞ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ​ውኑ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ።