የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሚልክያስ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ፥ ክንዳችሁን እገሥጻለሁ፥ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፣ ከእርሱም ጋር በአንድነት ትወሰዳላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ዘራችሁን እገሥጻለሁ፤ የመሥዋዕታችሁን ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ እናንተም ከርሱ ጋራ ትወገዳላችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፥ ዘራችሁን እገሥጻለሁ፥ በፊታችሁ ላይ ፈርስን እበትናለሁ፥ ይህም ፈርስ ለበዓላችሁ መሥዋዕት ካመጣችኋቸው ነው፤ እናንተንም ከእርሱ ጋር ያነሳችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በእናንተ ምክንያት ልጆቻችሁን እቀጣለሁ፤ ለመሥዋዕት ያመጣችኋቸውን እንስሶች እበት በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ ከፊቴም አስወግዳችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ፥ ክንዳችሁን እገሥጻለሁ፥ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፥ ከእርሱም ጋር በአንድነት ትወሰዳላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሚልክያስ 2:3
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚህ እነሆ፥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ መከ​ራን አመ​ጣ​ለሁ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ፤ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን ወንድ ድረስ አላ​ስ​ቀ​ር​ለ​ትም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ አል​ተ​ወ​ውም፤ ሰው ገለባ እስ​ኪ​ያ​ልቅ ድረስ እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድድ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ እሳ​ትን አነ​ዳ​ለሁ።


እነሆ ተደ​ላ​ድ​ያ​ለሁ በሚ​ል​በት ጊዜ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠ​ፋል። የሚ​ያ​ው​ቁ​ትም ወዴት ነው? ይላሉ።


እነ​ር​ሱስ ይህን አይ​ተው አደ​ነቁ፥ ደነ​ገጡ፥ ፈሩም።


ከአ​እ​ላፍ ይልቅ በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ችህ አን​ዲት ቀን ትሻ​ላ​ለች፤ በኃ​ጥ​ኣን ድን​ኳ​ኖች ከመ​ቀ​መጥ ይልቅ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እጣል ዘንድ መረ​ጥሁ።


የወ​ይ​ፈ​ኑን ሥጋ ግን፥ ቍር​በ​ቱ​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም ከሰ​ፈር ውጭ በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።


በወ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውና በአ​መ​ለ​ኳ​ቸው፥ በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና በፈ​ለ​ጓ​ቸው፥ በሰ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም፥ በሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ፊት ይዘ​ረ​ጓ​ቸ​ዋል፤ አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​ብ​ሯ​ቸ​ው​ምም፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ።


እር​ሻው ምድረ በዳ ሆኖ​አል፤ ምድ​ሪ​ቱም ታል​ቅስ፤ እህሉ ጠፍ​ቶ​አ​ልና፥ ወይ​ኑም ደር​ቆ​አ​ልና፥ ዘይ​ቱም ጐድ​ሎ​አ​ልና።


ጊደ​ሮች ከም​ሳ​ጋ​ቸው ጠፉ፤ ጎተ​ራ​ዎች ባዶ ሆኑ፤ ዐው​ድ​ማ​ዎ​ቹም ፈራ​ረሱ፤ እህሉ ደር​ቆ​አ​ልና።


እኔም እን​ዲህ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ፍር​ሀ​ትን፥ ክሳ​ት​ንም፥ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ፈ​ዝዝ፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ጠፋ ትኩ​ሳት አወ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም በከ​ንቱ ትዘ​ራ​ላ​ችሁ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችሁ ይበ​ሉ​ታ​ልና።


ርኵሰትንም በላይሽ እጥላለሁ፥ እንቅሽማለሁ፥ ማላገጫም አደርግሻለሁ።


ስለዚህ መንገዴን እንዳልጠበቃችሁ፥ በሕግም ለሰው ፊት እንዳዳላችሁ መጠን፥ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ አድርጌአችኋለሁ።


ለም​ድ​ርም ቢሆን፥ ለፍግ መቆ​ለ​ያም ቢሆን አይ​ረ​ባም፤ ነገር ግን ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ የሚ​ሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”


ይሰ​ድ​ቡ​ናል፥ እን​ማ​ል​ዳ​ቸ​ዋ​ለን፤ በዓ​ለም እንደ ጊጤ ሆን፤ በሁ​ሉም ዘንድ የተ​ና​ቅን ሆን።


ብዙ ዘርም ወደ እርሻ ታወ​ጣ​ለህ፤ አን​በ​ጣም ይበ​ላ​ዋ​ልና ጥቂት ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ።