የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሚልክያስ 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዔሳውን ግን ጠላሁ፤ ተራሮቹን ባድማ አደረግሁ፤ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮዎች ሰጠሁበት።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዔሳውን ግን ጠላሁት፤ ተራራውን አጠፋሁ፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች ሰጠኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዔሳውን ግን ጠላሁ፤ የዔሳውን ኰረብታማ አገር ወደ ምድረ በዳ ለወጥኩ፤ ምድሩንም የቀበሮ መፈንጫ አደረግሁት።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



ሚልክያስ 1:3
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አላት፥ “ሁለት ሕዝ​ቦች በማ​ኅ​ፀ​ንሽ አሉ፤ ሁለ​ቱም ሕዝብ ከሆ​ድሽ ይወ​ለ​ዳሉ፤ ሕዝ​ብም ከሕ​ዝብ ይበ​ረ​ታል፤ ታላ​ቁም ለታ​ናሹ ይገ​ዛል።”


ደረ​ቂቱ ምድር ኩሬ፥ የተ​ጠ​ማች ምድ​ርም የውኃ ምንጭ ትሆ​ና​ለች፤ የዎ​ፎች መኖ​ሪ​ያም ሸን​በ​ቆና ደን​ገል ይሆ​ን​በ​ታል።


እኔ ግን ዔሳ​ውን አራ​ቆ​ት​ሁት፤ የተ​ሸ​ሸ​ጉ​ት​ንም ስፍ​ራ​ዎች ገለ​ጥሁ፤ ይሸ​ሸ​ግም ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ዘሩም፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም፤ ጎረ​ቤ​ቶ​ቹም ጠፍ​ተ​ዋል፥ እር​ሱም የለም።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ የመ​ከ​ረ​ባ​ትን ምክር፥ በቴ​ማ​ንም በሚ​ኖሩ ስዎች ላይ ያሰ​ባ​ትን ዐሳብ ስሙ፤ ትን​ን​ሾች በጎ​ችን ዘር​ፈው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል፤ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ት​ንም ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ባድማ ያደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ዋል።


አሦ​ርም የወ​ፎች መኖ​ሪ​ያና የዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ ትሆ​ና​ለች፤ በዚ​ያም ሰው አይ​ኖ​ርም፤ የሰው ልጅም አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም።


ስለ ኤዶ​ም​ያስ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴ​ማን ጥበብ የለ​ምን? ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችስ ምክር ጠፍ​ቶ​አ​ልን? ጥበ​ባ​ቸ​ውስ አል​ቆ​አ​ልን?


እና​ንተ በድ​ዳን የም​ት​ኖሩ ሆይ! የዔ​ሳ​ውን ጥፋት፥ የም​ጐ​በ​ኝ​በ​ትን ጊዜ አመ​ጣ​በ​ታ​ለ​ሁና ሽሹ፤ ወደ ኋላም ተመ​ለሱ፤ በጥ​ል​ቅም ጕድ​ጓድ ውስጥ ተቀ​መጡ።


ባቢ​ሎ​ንም ባድ​ማና የቀ​በሮ ማደ​ሪያ፥ ማፍ​ዋ​ጫም ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ሰው አይ​ገ​ኝም።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም የፍ​ር​ስ​ራሽ ክምር፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ታው። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ልሽ ተፈ​ጸመ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ስ​ማ​ር​ክ​ሽም። የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ል​ሽን ይጐ​በ​ኘ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ት​ሽ​ንም ይገ​ል​ጣል።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ በአሉ አሕ​ዛብ ላይ እኔ እጄን አነ​ሣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ኀፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።


እነሆ እኔ ለእ​ና​ንተ ነኝና፤ ወደ እና​ን​ተም እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ትታ​ረ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ትዘ​ራ​ላ​ች​ሁም፤


በሀ​ገ​ራ​ቸው ንጹ​ሑን ደም አፍ​ስ​ሰ​ዋ​ልና በይ​ሁዳ ልጆች ላይ ስለ አደ​ረ​ጉት ግፍ ግብፅ ምድረ በዳ፥ ኤዶ​ም​ያ​ስም በረሃ ይሆ​ናል።


“በወ​ን​ድ​ምህ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ስለ ተደ​ረገ ኀጢ​አ​ትና ግድያ ኀፍ​ረት ይከ​ድ​ን​ሃል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ትጠ​ፋ​ለህ።


“ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ሊከ​ተ​ለ​ኝም የሚ​ወድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን፥ ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና እኅ​ቶ​ቹን፥ የራ​ሱ​ንም ሰው​ነት እንኳ ቢሆን የማ​ይ​ጠላ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።