የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እራ​ቴን አዘ​ጋ​ጅ​ልኝ፥ እስ​ክ​በ​ላና እስ​ክ​ጠጣ ድረ​ስም ታጥ​ቀህ አሳ​ል​ፍ​ልኝ፤ ከዚ​ህም በኋላ አንተ ብላ፥ ጠጣም ይለው የለ​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚህ ይልቅ፣ ‘እራቴን እንድበላ አዘጋጅልኝ፣ እኔ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፤ ከዚያ በኋላ አንተ ደግሞ ትበላለህ፤ ትጠጣለህ’ አይለውምን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

‘የምበላውን እራቴን አሰናዳልኝ፤ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፤ በኋላም አንተ ብላና ጠጣ፤’ ይለው የለምን?

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይልቅስ፥ ‘በል! ራቴን አዘጋጅልኝ፤ እስክበላና እስክጠጣም አደግድገህ አገልግለኝ፤ ከዚህ በኋላ አንተ ደግሞ ትበላለህ፥ ትጠጣለህ’ ይለው የለምን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የምበላውን እራቴን አሰናዳልኝ፥ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፥ በኋላም አንተ ብላና ጠጣ የሚለው አይደለምን?

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 17:8
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም ብን​ያ​ምን ከእ​ነ​ርሱ ጋር በአ​የው ጊዜ የቤ​ቱን አዛዥ እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “እነ​ዚ​ያን ሰዎች ወደ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው፤ እር​ድም እረድ፤ አዘ​ጋ​ጅም፤ እነ​ዚያ ሰዎች በእ​ኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበ​ላ​ሉና።”


ዳዊ​ትም ከም​ድር ተነ​ሥቶ ታጠበ፤ ተቀ​ባም፤ ልብ​ሱ​ንም ለወጠ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገብቶ ሰገደ። ወደ ቤቱም መጣ፦ እን​ጀ​ራም አም​ጡ​ልኝ አለ፤ በፊ​ቱም እን​ጀራ አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ በላም።


ጌታ​ቸው በመጣ ጊዜ እን​ዲህ ሲያ​ደ​ር​ጉና ሲተጉ የሚ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አገ​ል​ጋ​ዮች ብፁ​ዓን ናቸው፤ እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወገ​ቡን ታጥቆ በማ​ዕድ ያስ​ቀ​ም​ጣ​ቸ​ዋል፤ እየ​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም ያገ​ለ​ግ​ላ​ቸ​ዋል።


“አራሽ ወይም ከብት ጠባቂ አገ​ል​ጋይ ያለው ከእ​ና​ንተ ማን ነው? ከእ​ር​ሻው በተ​መ​ለሰ ጊዜ ጌታው ና፥ ፈጥ​ነህ ወደ​ዚህ ውጣና ከእኔ ጋር በማ​ዕድ ተቀ​መጥ ይለ​ዋ​ልን?


እን​ግ​ዲህ ጌታው ያዘ​ዘ​ውን ሥራ​ውን ቢሠራ ለዚያ አገ​ል​ጋይ ምስ​ጋና አለ​ውን?


ራት ከሚ​በ​ሉ​በት ተነ​ሥቶ ልብ​ሱን አኖ​ረና ማበሻ ጨርቅ አን​ሥቶ ወገ​ቡን ታጠቀ።