የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በተ​ራው የክ​ህ​ነ​ትን ሥራ በሚ​ሠ​ራ​በት ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንድ ቀን ዘካርያስ በምድቡ ተራ፣ በእግዚአብሔር ፊት በክህነት በሚያገለግልበት ጊዜ፣

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት በክህነት ሲያገለግል፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ጊዜ የዘካርያስ የክህነት ቡድን ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ተረኛ ነበር፤ ስለዚህ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት የክህነቱን አገልግሎት በመፈጸም ላይ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል፥

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 1:8
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ፥ በአ​ባ​ታ​ቸው በአ​ሮን እጅ እንደ ተሰ​ጣ​ቸው ሥር​ዐት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይገቡ ዘንድ እንደ እየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ቍጥ​ራ​ቸው ይህ ነበረ።


ናዳ​ብና አብ​ዩድ ግን ልጆች ሳይ​ወ​ልዱ ከአ​ባ​ታ​ቸው በፊት ሞቱ፤ የአ​ሮን ልጆች አል​ዓ​ዛ​ርና ኢታ​ም​ርም ካህ​ናት ሆነው አገ​ለ​ገሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህ​ናት እን​ዳ​ይ​ሆኑ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና ልጆቹ አስ​ለ​ቅ​ቀ​ዋ​ቸው ነበ​ርና ሌዋ​ው​ያን መሰ​ም​ሪ​ያ​ቸ​ውን ትተው ወደ ይሁ​ዳና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።


ክህ​ነት ለሚ​ገ​ባ​ቸው ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ዙሪያ ባሉ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ችና በሌ​ሎ​ችም ከተ​ሞች ላሉ ለወ​ን​ዶች ሁሉ፥ ከሌ​ዋ​ው​ያን ጋራ ለተ​ቈ​ጠሩ ሰዎ​ችም ሁሉ ከፍ​ለው ይሰጡ ዘንድ በስም የተ​ጠሩ ሰዎች ነበሩ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የካ​ህ​ና​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ሰሞን በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸ​ውና በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ በሮች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡና ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑም፥ ያከ​ብ​ሩም ዘንድ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን መደበ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ዳዊት እን​ዲህ አዝዞ ነበ​ርና ካህ​ና​ቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥር​ዐት በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሰሞን ከፈ​ላ​ቸው፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ፥ በካ​ህ​ና​ቱም ፊት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው፤ በረ​ኞ​ቹ​ንም ደግሞ በየ​በሩ ሁሉ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው።


በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ካህ​ና​ቱን በየ​ማ​ዕ​ር​ጋ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አቆሙ።


“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ​ተህ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅ​ርብ፤ አሮ​ንን የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች፥ ናዳ​ብን፥ አብ​ዩ​ድ​ንም፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ኢታ​ም​ር​ንም አቅ​ርብ።


ይህ​ንም ሁሉ ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታነ​ጻ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለህ።


“እኔ​ንም በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ሁለት አውራ በጎች ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም እቀ​ድ​ሳ​ለሁ፤ በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም ታስ​ታ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቆብ​ንም ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐ​ትም ክህ​ነት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም የአ​ሮ​ን​ንና የል​ጆ​ቹን እጆች ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።


በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን ቅባ​ቸው፤ ቀድ​ሳ​ቸ​ውም።


አን​ተም ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ እንደ መሠ​ዊ​ያ​ውና፥ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ እን​ዳ​ለው ሥር​ዐት ሁሉ ክህ​ነ​ታ​ች​ሁን ጠብቁ፤ የሀ​ብተ ክህ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ከሌ​ላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀ​ርብ ይገ​ደል።”


በይ​ሁዳ ንጉሥ በሄ​ሮ​ድስ ዘመን ከአ​ብያ ክፍል የሆነ ዘካ​ር​ያስ የሚ​ባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስ​ቱም ከአ​ሮን ልጆች ወገን ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ኤል​ሳ​ቤጥ ነበረ።


ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።