የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በራሱ ላይ አክ​ሊል አደ​ረ​ገ​ለት፤ በአ​ክ​ሊ​ሉም ላይ በፊቱ በኩል የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን የወ​ርቅ መር​ገፍ አደ​ረገ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት፣ ሙሴ መጠምጠሚያውን በአሮን ራስ ላይ አደረገ፤ በመጠምጠሚያው ላይ በፊት ለፊቱ በኩል የተቀደሰውን የወርቅ አክሊል አደረገለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያውን አደረገ፤ በመጠምጠሚያውም ላይ በፊቱ በኩል፥ የወርቅ ጉንጉን ሆኖ በቅጠል መልክ የተሠራውን የተቀደሰ አክሊል፥ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በራሱም ላይ ጥምጥም አደረገለት፤ በጥምጥሙም ላይ ከፊት ለፊት በኩል እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በወርቅ አጊጦ የተሠራውን የቅድስና ምልክት የሆነውን አክሊል አኖረ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያውን አደረገ፤ በመጠምጠሚያውም ላይ በፊቱ በኩል የተቀደሰውን አክሊል፥ ቅጠል የሚመስለውን የወርቅ ምልክት፥ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 8:9
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ልብ​ሶች እነ​ዚህ ናቸው፤ ልብሰ እን​ግ​ድዓ፥ ልብሰ መት​ከፍ፥ ቀሚ​ስም፥ ዥን​ጕ​ር​ጕር እጀ ጠባብ፥ መጠ​ም​ጠ​ሚያ፥ መታ​ጠ​ቂ​ያም፤ እነ​ዚ​ህ​ንም በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን፥ ለል​ጆ​ቹም የተ​ቀ​ደሰ ልብስ ያድ​ርጉ።


አክ​ሊ​ል​ንም በራሱ ላይ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የወ​ር​ቁ​ንም ቀጸላ በአ​ክ​ሊሉ ላይ ታኖ​ራ​ለህ።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፤ እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹ​ንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አው​ራ​ውን በግ ሁሉ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ይህ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን ነበረ።


አሮ​ንና ልጆ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ።


ደግሞ፦ ንጹሕ ጥምጥም በራስ ላይ አድርጉ አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፣ የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር።