ሕዝቅያስም፥ “አሁን እጃችሁን ለእግዚአብሔር አንጽታችሁ ቅረቡ፤ መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ” ብሎ ተናገረ። ጉባኤውም መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጡ፤ ልባቸውም የፈቀደ ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አመጡ።
ዘሌዋውያን 7:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘አንድ ሰው ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሊከተለው የሚገባው ሥርዐት ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሰው ለጌታ የሚያቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእግዚአብሔር ስለሚቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ነው። |
ሕዝቅያስም፥ “አሁን እጃችሁን ለእግዚአብሔር አንጽታችሁ ቅረቡ፤ መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ” ብሎ ተናገረ። ጉባኤውም መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጡ፤ ልባቸውም የፈቀደ ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አመጡ።
ከእስራኤል ማሰማርያ ከመንጋው ከሁለት መቶው አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ፤ ይህ ኀጢአታችሁን ያስተሰርይላችሁ ዘንድ ለእህል ቍርባንና ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለደኅንነትም መሥዋዕት ይሆናል” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በዘይትም የተለወሰው ወይም የደረቀው የእህል ቍርባን ሁሉ ለአሮን ልጆች ሁሉ ይሆናል፤ ለእያንዳንዱም እኩል ይሆናል።
“የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ ለእግዚአብሔር የደኅንነት መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ቍርባኑን ለእግዚአብሔር ከደኅንነቱ መሥዋዕት ያመጣል።
የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ የድኅነት መሥዋዕታችሁንም አልመለከትም።
ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች አቀረበ፤ የሰገር ልጅ የናትናኤል መባ ይህ ነበረ።