የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 27:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ የሚ​ያ​ቀ​ር​በው እን​ስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእ​ነ​ዚህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ሰውየው የተሳለው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሆኖ መቅረብ የሚችል እንስሳ ከሆነ፣ እንዲህ ያለው ለእግዚአብሔር የተሰጠ እንስሳ የተቀደሰ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ለጌታም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው እንስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእነዚህ ለጌታ የሚሰጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ስእለቱ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበው እንስሳ ከሆነ አይዋጅም፤ ለእግዚአብሔር የቀረበው መባ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለእግዚአብሔርም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው እንስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእነዚህ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 27:9
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰው ከገንዘቡ በችኮላ የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ይሆንበታል።


ለሥ​ጋህ በደል አፍ​ህን አት​ስጥ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት፥ “ባለ​ማ​ወቅ ነው” አት​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ቃልህ እን​ዳ​ይ​ቈጣ፥ የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ብህ፤


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ነውና ከእ​ርሱ ምንም አይ​ሸ​ጡም፤ አይ​ለ​ው​ጡ​ምም፤ የም​ድ​ሩም ቀዳ​ም​ያት አይ​ፋ​ለ​ስም።


መል​ካ​ሙን በክፉ፥ ክፉ​ው​ንም በመ​ል​ካም አይ​ለ​ውጥ፤ እን​ስ​ሳ​ንም በእ​ን​ስሳ ቢለ​ውጥ እር​ሱና ልዋጩ የተ​ቀ​ደሱ ይሆ​ናሉ።


ለግ​ምቱ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውን ቢያጣ ግን በካ​ህኑ ፊት ይቁም፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለ​ውን ሰው ከእጁ ባለው ገን​ዘብ መጠን ይገ​ም​ት​ለት፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለው ሰው እን​ደ​ሚ​ችል መጠን ይገ​ም​ት​ለት።


“ሰው ቢዘ​ነጋ፥ ሳያ​ው​ቅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ቀ​ደ​ሰው በማ​ና​ቸ​ውም ነገር ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ን​ጋዉ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።


እናንተ ግን ‘አባቱን ወይም እናቱን “ከእኔ የምትጠቀምበት መባ ነው የሚል ሁሉ፥