እኔም “እናንተ ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል፤ ዕቃዎቹም ቅዱሳን ናቸው፤ ብሩና ወርቁም ለአባቶቻችን አምላክ ለእግዚአብሔር በፈቃድ የቀረበ ነው፤
ዘሌዋውያን 22:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህ በላቸው፦ ማናቸውም ሰው ከዘራችሁ በትውልዳችሁ ርኵሰት እያለበት የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር ወደሚቀድሱት ወደ ቅዱስ ነገር ቢቀርብ፥ ያ ሰው ከፊቴ ተለይቶ ይጥፋ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲህም በላቸው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ ያልሆነ ማንኛውም ሰው፣ እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ለይተው ወዳቀረቡት ቅዱስ መሥዋዕት ቢቀርብ ያ ሰው ከፊቴ ይወገድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ በላቸው፦ ‘በትውልዳችሁ ማናቸውም ሰው ከዘራችሁ ሁሉ ርኩሰት እያለበት የእስራኤል ልጆች ለጌታ ወደሚቀድሱት ወደ ቅዱሳን ነገሮች ቢቀርብ፥ ያ ሰው ከፊቴ ተለይቶ ይጥፋ፤ እኔ ጌታ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከልጅ ልጆቻችሁ መካከል የረከሰ ሆኖ ሳለ የእስራኤል ልጆች ለእኔ ለይተው ወዳቀረቡት ቅዱስ ስጦታ ደፍሮ ቢቀርብ ከፊቴ ተወግዶ ይጠፋል፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ተጠብቆ ይኖራል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህ በላቸው፦ ማናቸውም ሰው ከዘራችሁ በትውልዳችሁ ርኩሰት እያለበት የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር ወደሚቀድሱት ወደ ቅዱስ ነገር ቢቀርብ፥ ያ ሰው ከፊቴ ተለይቶ ይጥፋ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
እኔም “እናንተ ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል፤ ዕቃዎቹም ቅዱሳን ናቸው፤ ብሩና ወርቁም ለአባቶቻችን አምላክ ለእግዚአብሔር በፈቃድ የቀረበ ነው፤
“የእስራኤል ልጆች ለእኔ ከሚቀድሱአቸው ከቅዱሳን ነገሮች ራሳቸውን እንዲለዩ፥ የተቀደሰውንም ስሜን እንዳያረክሱ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
የሞተውን ሰው በድን የነካ ሁለመናውን ባያነጻ የእግዚአብሔርን ድንኳን ያረክሳል፤ ያ ሰው ከእስራኤል ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ በእርሱም ላይ የሚያነጻ ውኃ አልተረጨምና ርኩስ ይሆናል፤ ርኵሰቱ ገና በእርሱ ላይ ነው።
በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።